😇 እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ 🧕 ከእናቱ ከድንግል ማርያም እና ቤተሰቡ ጋር ወደ ግብጽ (የአባይ/ጊዮን ወንዝ ውሃ) ሲሰደዱ ጌታችን በጥቂት ሳምንታት እና ከጥቂት ወራት መካከ ሳይሆን አይቀርም እድሜው። መስከረም አንድ/፩ (እንቍጣጣሽ) ከሆነ የጌታችን ልደት የሦስት ወር ሕፃን ነበር ማለት ነው።
ከሃያ አራት ዓመታት በፊት በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ የአዲስ ዓመት ዕለት (ምናልባትም የጌታችን የልደት ቀን) ዛሬ መሀመዳዊን ከንቲባ የመረጡባትን ኒው ዮርክ ከተማን ኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ (የዘመናችን ሄሮድሳውያን) ይህን ዕለት ለሽብር ጥቃት የመረጡትም በዚህ ምክኒያት መሆኑ እርግጠኛ መሆን ይቻላል።
በአውሮፓም መስከረም 11 (መስከረም ፩) ቀን በአውስሪያዋ ቪየና በዋነኝነት የሚታወቅበት ምክኒያት እ.ኤ.አ. መስከረም 11 ቀን 1683 (መስከረም ፫) ላይ የካሂንበርግ ጦርነት የሚመራው የኦቶማን ቱርክ ጦር ሰራዊት ሽንፈት በሁለተኛው የቱቶማን ጦርነት ውስጥ ወደ ኦቶማን ጦር ሽንፈት አመጣበት። ይህ አስተባባሪነት የተባበሩት መንግስታት ክርስቲያን ወታደሮች ኃይል በጀግናው የፕላንዱ ክርስቲያን ንጉሥ ዮሃን ሶቢየስኪ III መሪነት ስር የቪየና ከተማን ክፉኛ ከበባ ያቆመበት እና የክርስቶስ ተቃዋሚ ኦቶማን ቱርክ ግዛት ወደ አውሮፓ መስፋፋት ያቆመበት ቍልፍ ዕለት ተደርጎ ይቆጠራል።
ለኢትዮጵያ ብሎም ለመላዋ አፍሪካ ዛሬ የሚያስፈልጋት እንደ ፖላንዱ ንጉስ ሶቢየስኪ መስቀሉን ተሸክሞና ቅድስት ማርያምን እና ቅዱሳኑን አስከትሎ የኢትዮጵያን ጠላቶች ለመስቀል ጦርነት የሚነሳ ክርስቲያን ንጉሥ ብቻ ነው። ይህ ንጉሥ ደግሞ ከአክሱም ጽዮን ይነሳል የሚል ተስፋ አለኝ።
የሚገርም ነው፤ የግሪጎሪያኑ/አውሮፓዋኑ መስከረም 11 እና የኢትዮጵያ መስከረም ፩/1 በአንድ ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ መዋል የጀመሩት እ.አ.አ በ 1803 (መስከረም ፩/ 1፣ ፲፯፻፺፮/1796 ዓ.ም)ላይ ነው። በእሑድ ዕለት!
🧕 ኀዳር ፮ ቀን እመቤታችን ወደ ግብጽ አገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል አገር ገብታ ያረፈችበት በዓል ነው፡፡ ከገነት የተሰደደውን አዳም ወደ ገነት ለመመለስ ሲል ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ከአረጋዊው ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡ ጌታችን ከ፫/3 ዓመት ከ፮/6 ወር የግብጽ ስደት በኋላ ወደ እስራኤል እንደሚመለስ አስቀድሞ ነቢየ ልኡል ሆሴዕ በትንቢት መነጽርነት ተመልክቶ “ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት ” ብሎ ተናግሯል ሆሴ ፲፩፥፩
እንኳን አደረሰን!
💭 ከምወዳቸውና ከሚናፍቁኝ ውብ የአዲስ አበባ ዓብያተ ክርስቲያናት መካከል እንጦጦ ቁስቋም ማርያም መስከረም ፳፻፲ ወ ፩ /2011 ዓ.ም
ስለ መንበረ ንግስት ቁስቋም
ለእግዝአብሔር ካላቸው አክብሮትና ፍርሀት ለቤተ ክርስቲያንና በንግሥና ለሚያስተዳድሩት ህዝብ ካላቸው ፍቅር የተነሣ በህዝቡ “እምዬ” የሚል ስም የተሠጣቸው ንጉሠ ነገሥት አፄ ሚኒሊክ ከባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ጋር ሠራዊታቸውን አስከትለው ከእንጦጦ ቤተ መንግስታቸው ወደ ፍልውሃ እና ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሲንቀሣቀሱ መንበረ ንግስት ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን በታነፀችበት ሥፍራ ላይ ድንኳናቸውን ተክለው ቆይታ ያደርጉበት ነበር፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን እረፍት ባደረጉበት ሥፍራ እንቅልፍ ሸለብ ያደርጋቸውና አንዲት እጅግ የተዋበች ሴት ልጅ አዝላ በእቴጌ ጣይቱ አማሣል “ይህንን ቦታ ልቀቁልኝ፤ ቤቴን ልስራበት !!” ስትላቸው ያያሉ፡፡ ንጉሡም ከእንቅልፋቸው በመንቃት ያዩትን ሁሉ ለባለቤታቸው ለእቴጌ ጣይቱ ብጡል ይነግሯቸዋል፤ በመቀጠልም በእቴጌ ጣይቱ አምሣል ስለታየቻቸው በስምሽ ሆስፒታል ትሰሪበት ዘንድ ፈቅጄልሻለሁ ብለው ቦታውን ለእቴጌ ጣይቱ ይሰጧቸዋል፤ ከግዜ በኃላ ንጉሠ ነገሥት አፄ ምኒሊክ ስለታመሙ እቴጌ ጣይቱ ባለቤታቸውን ማስታመም ይጀምራሉ፤ አብረዋቸው አባታቸውን ያስታምሙ ለነበሩት ንግሥተ ነገሥት ዘውዲቱ አፄ ምኒሊክ ንጉሡ ያዩትን ራዕይና ሀኪም ቤቱን ለመስራት ያለመቻላቸውን ጭምር ይነግሯቸዋል፡፡ ከጥቂት ዓመታት በኃላ ንጉሠ ነገሥት አፄ ምኒሊክ አርፈው እቴጌ ጣይቱም እንጦጦ በቤተመንግስት ተቀምጠው ከእምዬ ምኒሊክ ጋር ያሣለፉትን ህይወት በማስታወስ አዲስ አበባን ቁልቁል እየተመለከቱ “ነበር እንዲህ ቅርብ ነው ወይ አሉ ይባላል !!” ብዙም ዓመት ሳይቆዩ እቴጌም ባለቤታቸውን ተከትለው አረፉ፡፡
ልጅ ኢያሱ መሪነቱን ይዘው በነበሩበት ሠዓት ከመኳንንቱ፤ መሳፍንቱ እና ሹማምንቱ ጋር በአስተዳደር ባለመግባባታቸው ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ሚኒሊክን ንግሥናቸውን እንዲረከቡ ሲደረግ ራስ ተፈሪ መኰንን አልጋወራሽነትን እንዲረከቡ ተደረገ፡፡ የንግሥና ህይወታቸውን ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ሚኒሊክ በመባል በትረ መንግስታቸውን ከተረከቡ በኃላ እቴጌ ጣይቱ የነገሯቸውን አስታውሰው፤ ዛሬ መንበረ ንግስት ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን በተተከለችበት ቦታ ላይ ሆስፒታሉን ለመሥራት የመሠረት ቁፋሮ ይጀመራል፡፡ በቁፋሮውም ወቅት አስደናቂ ነገር ይከሠታል፤ ይኽውም “ታቦተ ቁስቋም የሚል ፅሑፍ ያለበት የንግሥት እሌኒ የመዳብ ወንበር እና የብረት መስቀል” ይገኛል፡፡ ንግሥት እሌኒ የአፄ ዘርዓያቆብ እህት ሲሆኑ በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ ንግሥናቸውም በ1426 ዓ/ም እንደነበረ የኢትዮጵያ ታሪክ ያስረዳናል፡፡ የ492 ዓመት ዕድሜ ያለው ንብረት ከመሬት ተቀብሮ በጥበብ እግዚአብሔር ተጠብቆ ምንም ሳይበላሽ መገኘቱ ድንቅ የእግዝአብሔር ሥራን ያመላክተናል፡፡ በዚህም ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ተደንቀው ንዋየ ቅዱሣቱን መስቀል እና ሌሎቹንም የተገኙትን በታሪከ ነገሥታት በዓታ ለማርያም እንዲቀመጥ ያደርጋሉ፡፡ በቁፋሮው ግዜ በተገኘው ንዋየ ቅዱሣት ምክንያት ሥራው ወደ ተቋረጠው የሆስፒታል ቦታ በመሄድ ቤተክርስቲያን ይሠራ ዘንድ ሕዳር 6 ቀን 1918 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡ መቃኞውም በአስቸኳይ ይሠራ ዘንድ ለራስ ዳምጠው ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡
በበጎ ሥራቸውና ካህናትን በመውደዳቸው ምክንያት ዘመነ ካህናት ተብሎ በሚጠራበት ግዜ በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ሚኒሊክ ዘመነ ንግሥና በግብፃዊው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ ፍፃሜ ዘመን በሰሜን አዲስ አባባ ልዩ ስሙ እንጦጦ በተባለ ስፍራ በራስጌ ርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም እና ደብረ ኃይል ቅዱስ ዑራኤል ወቅዱስ ኤልያስ በግርጌ ሀመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነ ምህረት እና ቀጨኔ ደብረ ሠላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያንን አዋሣኝ አድርጋ በመሐል ባለ ልዩ ጉብታ (መሶብ) በምትመስል በግማሽ አዲስ አባባን ሊያሣይ በሚችል ቦታ ላይ መቅደስና ቅኔ ማህሌት ያለው መቃኞ ቤተክርስቲያን ሠርተው በትእዛዙ መሠረት አሠርተው ታቦተ ቁስቋም ማርያምንና ታቦተ መድኃኔዓለም ኢየሱስን ሌሎችንም ንዋየ ቅዱሳት በእጨጌ ተድላና በዓቃቤ ሠአት መምሬ አበበ ትዕዛዝ በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ሚኒሊክ መኪና በካህናትና ዲያቆናት በምዕመናንና ምዕመናት ታጅቦ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ እና ታላላቅ ሹማምንት በተገኙበት በግብፃዊው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ ባራኪነት ታቦ ኅዳር 6 ቀን 1919 ዓ.ም ገባች፡፡ ስያሜዋንም “መንበረ ንግሥት ቁስቋም ማርያም” ብለዋታል፤ የመጀመሪያው አስተዳዳሪም ቄስ ገበዝ ብሥራት ኃ/ማሪያም ነበሩ።
No comments:
Post a Comment