https://www.bitchute.com/video/5lkPo8oIrLVD/
✞ የጌታችን ስቅለት | በዚያን ዕለት የከርስቶስ ልጆች ክርስቲያን፤ የክርስቶስ ተቃዋሚው ልጆች እስላም ተባሉ
❖ ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ "የድኅነት ቀን" ይባላል፡
✞ ፲፫ቱ ሕማማተ መስቀል
፩ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
፪ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
፫ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይ መውደቅ)
፬ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ)
፭ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም)
፮ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
፯ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
፰ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
፱ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
፲ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
፲፩ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
፲፪ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይ መሰቀል)
፲፫ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት)
✞ ጌታችን ሲሰቅል የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል፤
፩. ፀሐይ ጨለመ፤
፪. ጨረቃ ደም ኾነ፤
፫. ከዋክብት ረገፉ፤
፬. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤
፭. አለቶች ተፈረካከሱ፤
፮. መቃብራት ተከፈቱ፤
፯. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩-፶፬)፡፡
✞ ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል፤
፩. "ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)"፤
፪. "እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ"፤
፫. "አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው"፤
፬. እመቤታችንን "ሴትዮ ሆይ፣ እነሆ ልጅሽ"፤ ደቀ መዝሙሩንም "እናትህ እነኋት" በማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤
፭. "አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ"
፮. "ተጠማሁ"፤
፯. "ዅሉ ተፈጸመ" (ማቴ. ፳፯፥፵፭-፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫-፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲-፴)፡፡
ከሰድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጨለማ ኾኖ ከቈየ በኋላ ከዘጠኝ እስከ ማታ እንደ ተለመደው ብርሃን ሁኖአል፡፡ "ወፍና ሠርክ ይበርህ ብርሃነ ፀሐይ" እንዲል (ዘካ. ፲፬፥፯)፡፡ በዚህ ዕለት ሰባት መስተፃርራን (ጠበኞች) ታረቁ፤ ተስማሙ፡፡ እነዚህም፡- ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሕዝብና አሕዛብ፣ ነፍስና ሥጋ ናቸው (ኤፌ. ፪፥፲፤ ቈላ. ፩፥፳)፡፡ ጌታችን ጠዋት በሦስት ሰዓት ተገረፈ፤ በስድስት ሰዓት ተሰቀለ (ማቴ. ፳፯፥፩-፴፯፤ ሉቃ. ፳፫፥፩-፵፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፩)፡፡
ጌታችን በውኃው ተጠምቀን፣ ደሙን ተቀብለን የእግዚአብሔር ልጆች እንኾን ዘንድ ከቀኝ ጎድኑ ጥሩ ውኃ፣ ትኩስ ደም አፈሰሰልን (ዮሐ. ፲፱፥፴፬)፡፡ በዐሥራ አንድ ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከመስቀል አውርደው ሽቶ እየረበረቡ በድርብ በፍታ ገንዘው ቀበሩት (ሉቃ. ፳፫፥፶-፶፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፴፰-፵፪)፡፡ ነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዳ ነፍሳትን ነጻ አወጣች (፩ኛ ጴጥ. ፫፥፲፱)፡፡ በዚህ ጊዜ በርሃነ መለኮቱ በሲኦል ተገለጠ፡፡ ስለዚህም "ንሴብሖ ለእግዚአብሔር" እየተባለ ይዘመራል፡፡ ከሆሣዕና አንሥቶ ተከልክሎ የነበረው ኑዛዜ ይናዘዛል፤ ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል፡፡
ጌታም ቆላተ ዮሳፍጭ ከሚባል በረሀ አውርዶ መናውን ውሀውን ከወትሮ አብልጦ አወረደላቸውና ኃይሉን ከሂሎቱን አሳይቶ ወእንዘ ዓዲ መብልዖሙ ውስተ አፋሆሙ ነዘር እባብ አስንቶ ጐዳናቸውን እየስቀደደ አስፈጃቸው። ሙሴም አቤቱ ጌታዬ አሕዛብ ፳ኤልን የሚመግባቸው ቢያጣ ከበረሀ አውርዶ አስፈጃቸው እንዳይሉህ መድኃኒት ፈልግላቸው ብሎ ጸለየ። ጌታም የወዳጁን ጸሎት ፈጥኖ ይሰማልና ብርቱን እባብ አስመስለህ በተራራ ላይ ተራዳ ተክለህ ብርቱን በዚያ ላይ ሰቅለህ አሳያቸው ያን አይቶ ሰምቶ ያመነ ይዳን ያላመነ ይፈጸም አለው። ተራራው በቀራንዮ አምሳል ነው፤ ተራዳው የመስቀል ብርቱ የወልደ እግዚአብሔር እባብ የዲያብሎስ ቍስሉ የኃጢአት መርዙ የመርገመ ሥጋ የመርገመ ነፍስ በረኃው የገሃነም እሳት አምሳል ነው።
ያን አይተው ሰምተው ይዳኑ ማለት ስቅለተ ክርስቶስን አይተው ያመኑ ሐዋርያት፣ ሰምተው ያመኑ ምዕመናን የመዳናቸው አምሳል ነው። ያላመኑ ይፈጸሙ ማለቱ፡ ስቅለተ ክርስቶስን አይተው ያላመኑ አይሁድ ሰምተው ያላመኑ አይሁድ፣ ሰምተው ያላመኑ አሕዛብ ያለመዳናቸው አምሳል ነው።
ነፍስ ያለው እባብ የገደላቸውን ሰዎች ነፍስ የሌለው ብርት እንዳዳናቸው በባሕርዩ ሞት የሌለበት አምላክ ዲያብሎስ ያስገራቸውን ነፍሳት ተሰቅሎ ሞቶ የማዳኑ አምሳል ነው።
ጽዮን የተባለች ማኅፀነ ማርያም ደብረ መቅደሱ የተባለ አካሏ ነው።
ጌታም እነዚያ አላወቁም እንጂ እኔስ በማኅፀነ ማርያም አድሬ ለጻድቃን ለሰማዕታት ነገሥሁላቸው በአይሁድ በመናፍቃን ነገሥሁባቸው ሲል ነው። አንድም ጽዮን የተባለ መሰቀሉ ደብረ መቅደሱ የተባለ አካሉ ነው
እነዚያ አላወቁም እንጂ እኔስ በመስቀል ተሰቅዬ ለጻድቃን ለሰማዕታት ነገሥሁላቸው በአይሁድ
በመናፍቃን ነገሥሁባቸው ሲል ነው እንዲህ ፯ት ተአምራት ሲሠሩ አይተው የባሕርይ አምላክ ነው እንጂ የባሕርይ አምላክማ ካልሆነ እንዲህ ያሉ ተአምራት ባልተሠሩ ነበር ያሉ ክርስቲያን ተባሉ።
አምላክ አይደለም፣ አልተወለደም፣ አልተሰቀለም፤ የአምላክ ወዳጅ ደግ ሰው ነብይ ብቻ እንጂ ያሉት እስላም ተባሉ። እስላምና ክርስቲያን የተባለበት ያን ዕለት ነው።
አይሁድ ግን አላክም ነብይም አይደለም ሐሳዌ መሲሕ ነው ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለም ብለው ካዱት።
“መናፍቃን ካህናት አላውያን መኳንንት ከሀድያን ነገሥታት ሃይማኖታችሁን ጣሉ ፈጣሪያችሁን ካዱ ለጣኦት ስገዱ ብለው እንደ እኔ እራሳችሁን እየመቱ አክሊለ ሦክ ግንድ አሸክመው በብረት ቢቸነክሯችሁ መራር ሐሞት ቢያጠጧችሁ ዋጋችሁን በመንግሥት ተቀበሉት እንጂ ሃይማኖታችሁን አትጣሉ፤ ፈጣሪያችሁን አትካዱ፤ ለጣኦት አትስገዱ!” በማለት ጌታችን አስተምሮናል።
✞ ከፍኖተ መስቀሉ ከህያው ቅዱስ ቃሉ በረከት ይክፈለን
✞ Today millions of Orthodox Christians commemorate Good Friday, also known as “Great Friday” to remember the events leading up to Jesus' Crucifixion.
In Ethiopia, Good Friday is known locally as Siklet which translates to Crucifixion of the Lord Jesus Christ. It is a day of fasting, intense prayer and prostrations.
Followers of Ethiopian Orthodox Churches share the religious tradition with other Orthodox Churches. In Ethiopia, churches outside the Ethiopian Orthodox Church including Catholic celebrate the good Friday along with the Ethiopian Church.
Good Friday is the holiday that Lord and Savior Jesus Christ was crucified for the salvation of human race. He was beaten hard, spited on and dragged with a robe all the way through to Calvary.
After His capture betrayed by Judas on Thursday eve subsequent to His prayer in Gethsemane, the Jews took Him and started their torture. Early morning on this Holy Friday, Lord Jesus Christ was brought to trial in front of the Jewish leader Pilate. Convicted for a crime He did not commit, Lord Jesus was tortured and tormented until He reached to the Calvary for crucifixion. Upon it was revealed miracles including the darkening of the sun, the bleeding of the moon and the falling of the stars whilst Lord Jesus Christ separated His divine soul from His body at the ninth hour. Then after, Joseph and Nicodimus took His holy body and buried it.
✞ A chapter in one of the Prayer books (The Passion of Cross or Himamat Meskel) of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church teaches us the following very important lesson:
“They did not
know, but I was crucified and reigned over the righteous and the
martyrs, so the Jews who saw those 7 miracles being done, were called
Christians because they said that it could only be a God of nature
who is showing us these miracles, and if He was not a God of nature,
such miracles would not have been done.„
And,
☪ “Those who deny the divinity of Jesus by saying, „He is not God, He was not born, He is not The Son of God, God doesn't have a son, He was not crucified, He is only a friend of God, a good man and just a prophet; They are called Muslims, or followers of Islam. It was on that very day that Islam and Christianity were called as such.”
May God accept our prayer, fasting and all our endeavors on the great lent and redeem us; Amen!
The Good Friday procession of the Ethiopian Orthodox Church in Jerusalem | ስቅለት በኢየሩሳሌም
https://www.bitchute.com/video/HwTCCb7lHHqN/
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡