Showing posts with label Apostles. Matthew. Show all posts
Showing posts with label Apostles. Matthew. Show all posts

Wednesday, October 22, 2025

Apostle Matthew's Ethiopian Village | የሐዋርያው ማቴዎስ የኢትዮጵያ መንደር


https://www.bitchute.com/video/lTXhJVRYF3l0/

✞✞✞

ጥቅምት ፲፪/ 12፤ የሐዋርያውና ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ በዓለ ዕረፍቱ ነው፤ ከቅዱስ ማቴዎስ ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡

ሐዋርያ ቅዱስ ማቴዎስ የኢትዮጵያ ልዑል እና ጳጳስ

🥴 ለመሆኑ ለምንድን ነው በወንጌላውያኑ ቅዱስ ማቴዎስ እና ቅዱስ ሉቃስ ስም የሚጠራ ቤተ ክርስቲያን ወይንም ገዳም በሃገራችን ኢትዮጵያ የሌለው?! ምክኒያቱ ምን ይሆን? እኔ እስካሁን አላየሁም አልሰማውሁም፡ በወንጌላውያኑ ቅዱሳን ማርቆስ እና ዮሐንስ የተሰየሙ ዓብያተክርስቲያናት ግን አሉ።

አዲሱ የክርስቲያን ልዑል ማቴዎስ ህዝቡን ወደ እውነተኛው እምነት ለመለወጥ ህይወቱን ሰጥቷል። ብዙም ሳይቆይ ቅዱስ ፉልቪያን-ማቴዎስ አገዛዙን ተወ እና ቅስና ተሾመ። ኤጲስ ቆጶስ ፕላቶን ሲሞት ሐዋርያው ማቴዎስ ተገልጦለት ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ እንዲቀደስና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ራስ እንዲሆን አዘዘው። ኤጲስ ቆጶስ ከሆነ በኋላ፣ ቅዱስ ፉልቪያን-ማቲዎስ የሰማያዊ ረዳቱን ሥራ በመቀጠሉ በቀሪው የሕይወት ዘመኑ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ለአፍሪካ ሕዝቦቹ በመስበክ ደክሟል።

😇 ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ | በፍርድ ቀን፤ ከ፪ሺ ዓመት በኋላ፤ “ወንጌል አልተሰበከልንም” ማለት የለም

Journey of Apostle Matthew to Ethiopia | ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ በኢትዮጵያ

https://wp.me/piMJL-bH1

💭 ፊልሙን ከዚህ ጽሑፍ ጋር እናነጻጽረው፦

የዓለም መድኃኒት እየሱስ ክርስቶስ እኔን ማቴዎስን መርጦ ተከተለኝ አል እኔም ስላመነታ ተከተልኩት የመዳን ተስፋ የሆነውን የወንጌሉን ቃል እንድንሰማና ከእርሱ አፍ የሰማሁትንም ለዓለም እንዳሰማ ልኮኛል።

መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ሊያድን ከእግዚአብሔር አብ የመጣ ከእርሱም ሌላ አዳኝና መሐሪ ወደ እግዚአብሔር መንግሥትም የሚያገባ እንደሌለ የአየሁትን ልመሰክር የሰማሁትን ቃል ለእናንተ ለአሰማ ከቃሉ የተነሣ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ትሆኑ ዘንድ በስሙም ትጠመቁ ዘንድ ልኮኛል። ከአብና ከልጁም ከእኛም ህብረት እንዳላችሁ ያንጊዜ ታውቃላችሁ፤ ዓለሙ ግን የፈጠረውን ተጣሪውን ትቶ ላልፈጠረው ምህረት የአደረገለትን ጌታውን ትቶ ሥቃይንና መአትን ለሚያመጣበት ለክፉ መንፈስ እየተገዛና የክፉ መንፈስ ባሪያ በመሆን የኃጢአትን ንጉሥ ዲያብሎስን እያገለገለ ይገኛል።

ይህ ክፉ መንፈስ በሰዎች ልብ ላይ መርዙን እንደረጨ ሁሉ እንዲሁ በእግዚአብሔር ልጆች ላይ ደጋኑን ወጥሮ ቀስቱን እንደቀተረ ነው። አንዳንዶች ወገኖች ለእርሱ ሲማረኩለት ጥቂቶችም የሆኑ የእግዚአብሔር ምርጥ ሕዝቦች ከፍጹም እምነታቸውና ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የተነሣ በጸሎት ድል ያደርጉታል፡ በጾምም ያሸንፉታል ያሳፍሩታልም። ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣው ለእግዚአብሔር ልጅ ለእየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ሠራዊቱ ናቸው። መንፈሱን ተላብሰዋል፣ ጸጋውን ተሞልተዋል፣ ኃይሉንም ታጥቀውታል። ሥልጣንም በአፋቸው ተሰጥቷል። እኒሁ እናንተም የእግዚአብሔር አብን ምህረት የልጁንም የእየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ልትቀበሉትና ልትለብሱት ለመጣችሁ ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሁንላችሁ። የልጁም የእየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ይፅናላችሁ። አሜን።

እቴ ህንድኬ ዣን ንግሥተ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ በሆነች በአሥራ አንደኛው ዘመነ መንግሥትዋ ከእየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት አንዱ ቅዱስ ማቴዎስ በመርዌ ከተማ የሚኖሩትን ህዝቦች ቃለ ወንጌል እየሰበከ አስተምሮ ማጥመቁን ሰማች፤ ይዘውት ወደ እርስዋ እንዲመጡ መልእክተኞችን ወደ ወንጌላዊ ማቴዎስ ላከች፡ ነገር ግን ስለክርስቶስ መወለድና ብዙ ታእምራትንና ድንቅ የሆኑ ሥራዎችን እየሱስ ክርስቶስ መሥራቱን ሰምታ ስለነበረ የእየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ነው ሲሏት መልኩን ለማየት የሚያስተምረውንም ለመስማት ጓጉታ እርሱ የእግዚአብሔር አገልጋይ ከመምጣቱ እኔ መሄድ አለብኝ ብላ በብዙ ሺህ ሠራዊት ታጅባ ወደ መርዌ /መርዋ/ 70 .. ሄደች።

በዚያም ቅዱስ ማቴዎስን አግኝታ እንዲህ አለችው፦

እየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እኛ እንደተላከና የሰላም አለቃ የዘለዓለም አባት እንደሆነ ከነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተነሣ አምናለሁ፤ ነገር ግን በውኃ ጥምቀት ከእግዚአብሔር መወለድን የእግዚአብሔር ልጅ መባልን አላውቅም ነበር፡ አሁን ግን አንተን ወደ እኛ የላከህና ከአንተ ላይ የአለ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከስብከትህ የተነሣ ገለፀልኝ፡ የምትነግረን ቃለ ወንጌል ህይወት መድኃኒት እንደሆነ አወኩ በእርሱም አመንኩ ስለዚህ አጥምቀኝ።” አለችወ።

ቅዱስ ማቴዎስም እግዚአብሔር ወደ እርሱ እንደላካት አውቆ በደስታ ከሠራዊትዋ ጋር ወደ ግዮን ወንዝ ወረዱ ከዚያም ከእርሱዋ ጋር የነበረው ሠራዊትና መኳንንት ሁሉ በእየሱስ ክርስቶስ ስም አጠመቃቸው። እንዲህ ሲል፦

በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠቃችሁ አለሁ!” እያለ።

እቴ ህንደኬ ዣን እንደህዝብዋ ተጠመቀች፤ ፍጹም ክርስቲያን ሆነች፤ ከዚያም ቅዱስ ማቴዎስን ከደቀ መዛሙርቶቹ ጋር ወደ አክሱም አምጥታ አክሎስ የሚባለውን ባልዋን ልጆችዋን ቤተሰብዋን ሁሉ በእየሱስ ክርስቶስ ስም አስጠመቀች። ቅዱስ ማቴዎስ በአክሱም አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፤ ከበርቶሎሜዎስ ቀጥሎ ለመጀመሪያ ጊዜ የኑብያን፣ የኢትዮጵያንና የናግራንን ሰዎች የአጠመቀ ከአሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት አንዱ ወንጌላዊ ማቴዎስ ነው።

እንደዚህም ሆነ እቴ ህንደኬ ዣን ክርስቲያን በሆነች በአሥራ ሦስት አመትዋ አቡሳውያን /አበሾች/ የሚባሉት የአክሱም የአዶሊስ ሕዝቦችና ፈላስያን /ፈላሾች/ በሌዋውያን ምክር ወንድሙዋን ንጉሠ ባህር ዘዝቃሌስ ተብሎ የነበረውን ከተብን አፄ ባህር ሰገድ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ብለው በበላዩዋ ላይ አነገሡት፤ እቴ ህንደኬን ዣንና አክሎስ ልጆቸዋን ገድለው አቃጠሏት። እርሷም በሰማእትነት በሰማንያ ሦስት /83/ በነገሠች በ24 ዘመነ መንግሥቱዋ አረፈች።

አፄ ባህር ሰገድ ተብሎ በነገሠው በከተብ ዘመነ መንግሥት እየሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ክርስቶስ ተወልዶአል ብሎ የሚያስተምርና የሚአምን ሰው ቢገኝ እንዲገደል በአዋጅ ተነገረ።

የእስራኤል ልጆች የሆኑ ሌዋውያን ካህናት እየሱ ክርስቶስም አይደለም ስሙንም መድኃኒት አይደለም ለማለት “ኢየሱስ” እንጂ “እየሱስ” ብላችሁ አትጥሩ ብለው በምኩራብ በአደባባይ በቢተ መቅደስ በገበያ አስተማሩ።

እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆችን ጥጦስ የሚባለውን አስነስቶ በጭካኔ እንደገደላቸው ሁሉ እንዲሁ የባህር ሰገድን መርከብ ሠራተኞችና በአዶሊስ በዳህቂቅ የሚኖሩትን ቤተ እስራኤል ሂክሶስ የሚባሉት የግሪኮችን ሰዎች አስነስቶ አስገደላቸው።

ንጉሠ ነገሥቱ ባህር ሰገድ ክርስቶስ እየሱስ በተወለደ 105 መታራ ከሚባለው አገር ላይ ከግሪኮች ከሮማውያን ጋር ጦርነት አድርጎ ተማርኮ በ81 ዓመት እድሜው በነገሠ በ22 ዘመነ መንግሥቱ ሞተ።

አንዳንድ ጎሣዎችና በጎሣዎች ውስጥ የሚገኙ ነገዶች ቃለ ወንጌል ያልተሰበከላቸው በጨለማ ዓለም ውስጥ ከመኖራቸው የተነሣ ከንቱ የሆነ አምልኮት ያመልኩና ለሚያመልኩት ነገር እንስሳና አእዋፍ ዶሮ ያርዱለት ነበር። ከዚያም አልፈው ሰውን አስረው እንደ እንስሳ የሚያቀርቡና የሚሰው ነበሩ። የሚያመልኳቸው ተራራዎች ዛፎች ሸለቆዎች ኮረብታዎች አራዊቶች ነበሩ። እንደዚሁ አስቀያሚ መልክ ያላቸው ቅርጾችን ያመልኩባቸው ነበር።

ነገር ግን የሰው ልጅ ክቡር ፍጥረት እንደሆነ ከሁሉም በላይ መሆኑን የሚያምኑና ሁሉን የፈጠረና ቻይ ጌታ እግዚአብሔር ብቻ አንድ አምላክ እንደሆነ በነቢያት ላይ አድሮ ለሰው ልጆች ህግና ሥረአት እንዲኖራቸው የፈቀደ ወይም የአዘዘ ትእዛዙንም የሚፈጽሙ የመልከ ጼዴቅ ካህን ዘሮች የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው የሚጠሩ ኢትዮጵያውያን ብቻ ነበሩ። በኋላ ዘመን ደግሞ የአብርሃም ዘሮች በሙሴ አማካኝነት አንድ እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመሩ። ከዚህ በኋላ ነው ሁለቱ ጎሣዎች አንድ እግዚአብሔርን በማምለክና በማመን ሲኖሩ የአለም መድኃኒት እየሱስ ክርስቶስ በቤተ ልሔም በተወለደ ጊዜ ሊሰግዱለት ሄደው ከሌላው ዓለም በፊት የተገኙትና ገጸ-በርከት አቅርበው ወደ ሀገራቸው በሰላም የተመለሱ።

አሁንም እኛ ኢትዮጵያውያን የክርስቶስን ትእዛዝና ትምህርት የተቀበልን እንደ ኃዋርያት ማለት ብሉያት መጽሐፍትን አስቀድመን እንደተቀበልን፡ መጽሐፍተ አዲሳትንም ወዲያውኑ ነው የተቀበልንና አምነን በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስ ስም የተጠመቅነው፤ በስሙ ክርስቲያኖች የተባልነው እንጂ ሐዲሳትን መጻሕፍትን ብቻ እንደተቀበሉት እንደ አሕዛቦች አይደለም። ለዚህ ሁሉ ምስክራችን ፈጣሪያችን እግዚአብሔርና እግዚአብሔር ያዘዘው የአምልኮታችን ሥርአት ነው። እሄውም የማይታየው አምላክ በነቢያት ሰው እንደሚሆን አስቀድሞ መነገሩ በሐዋርያት ሰው መሆኑ መሰበኩን የሚያበስሩትን ብሉያትና ሐዲሳትን /በማስማማታችን/ በማዋሐዳችን እምነታችን ተዋሕዶ ሃይምንት ተብሏል። ምስጢሩም ቃል ሥጋ በመሆኑ የነቢያት ትንቢት በመፈጸሙ ተዋሕዶ ሃይማኖት አሰኝቶታል።

እሄን ክብርና ጸጋ ለሰጠን ለአንድ እግዚአብሔር የአምልኮት ምስጋናና ሥግደት ይገባዋል። እግዚአብሔር ለዘለዓለም ለሰው ልጆች ሰላምንና ፍቅርን ሕብረትንም ይስጠን። ምህረቱና ቸርነቱም በሰማይ እንደሆነ በምድርም ይሁን። አሜን።

Apostle Saint Matthew († First Century) PRINCE & BISHOP OF ETHIOPIA

St. Matthew The Apostle of Ethiopia | ቅዱስ ማቴዎስ ዘኢትዮጵያ

https://wp.me/piMJL-bH7

https://www.bitchute.com/video/pJcsubd9VrP9/

The new Christian Prince Matthew dedicated his life to converting his people to the True Faith. Soon St. Fulvian-Matthew abdicated his rule and was ordained a priest. Upon the death of Bishop Platon, the Apostle Matthew appeared to him and instructed him to be consecrated as Bishop and to be the head the Ethiopian Church. Having become a bishop, St. Fulvian-Matthew labored at preaching the Word of God to his African people for the rest of his life, continuing the work of his heavenly patron.

Saint Matthew the Evangelist, was martyred today, on Tikmet 12 / October 22. He was one of the Twelve Disciples and his name was Levi. He was the one sitting at the receipt of custom outside the city of Capernaum, when the Lord Christ said to him, “Follow Me.” He left all, rose up, and followed Him. He made for the Lord Christ a great feast in his own house. That made the Pharisees murmur against Him saying to His disciples, “Why do your teacher eat and drink with tax collectors and sinners?” Jesus answered and said to them, “Those who are well do not need a physician, but those who are sick. I have not come to call the righteous, but sinners to repentance.” (Luke 5:27-32)

He preached in the land of Palestine and Tyre and Sidon. Then he went to Ethiopia. He entered the city of priests and converted them to the knowledge of God. When he wished to enter the city, he met a young man who told him, “You will not be able to go in unless you shave off the hair of your head and carry palm branches in your hand.” He did as the young man told him. And, as he was thinking about that, the Lord Christ appeared to him in the form of the young man who had met him earlier, and after He encouraged and comforted him, disappeared. He realized that this young man was the Lord of Glory Himself.

He then entered the city as one of its priests. He went to the temple of Apollo and found the high priest, and talked with him concerning the idols that they were worshipping. He explained to him how those idols did not hear or sense anything and how the true Mighty Lord is He who created the Heaven and Earth. The Lord made through him a wonder: a table came down to them from Heaven and a great light shone around them. When Hermes the priest saw this wonder, he asked him, “What is the name of your God?” The apostle replied, “My God is the Lord Christ.” Hermes, the priest, believed in Christ and many people followed him.

When the Governor of the city knew that, he ordered them burned. It happened at that time that the son of the Governor died. Saint Matthew the Apostle prayed and made supplications to God to raise the son and the Lord answered him and raised the child from death. When the Governor saw that, he and the rest of the people of the city believed. Saint Matthew baptized them and ordained a bishop and priests, and built a church for them.

After he had preached in other countries, he went back to Jerusalem. Some of the Jews which had been preached to, and had believed and been baptized by him, asked him to write down what he had preached to them. He wrote the beginning of the Gospel attributed to him in the Hebrew language but he did not complete it. It was said that he finished it during his preaching in India, in the first year of the reign of Claudius and the ninth year of the Ascension.

His martyrdom was consummated by stoning by the hands of Justus the Governor, and his body was buried in Carthage of Caesarea by some believers, in a holy place.

May Saint Matthew’s prayer be with us, Amen!

The Romanian People Achieved a Miracle: The Most Imposing Orthodox Cathedral In The World

https://www.bitchute.com/video/7lljM33AsBUX/ https://rumble.com/v70uys8-the-romanian-people-achieved-a-miracle-the-most-imposing-orthodox-c...