https://www.bitchute.com/video/3YIl9lLbY4GW/
✞ መስከረም ፲፮/16 ቀን ደገኛዋ እናት እሌኒ ቅድስት ደመራ ደምራ በደመራው ጢስ አማካኝነት
የተቀበረበትን ቦታ አገኘች መስከረም ፲፯/ 17 ቁፋሮ ጀመረች፤ ከ ፫፻/300 ዘመናት በላይ ቆሻሻ እየተጣለበት ታላቅ ተራራ አህሎ ነበርና እነሆ ቁፋሮ ስድስት ወራት ፈጀባቸው መጋቢት 10 በዛሬዋ ቀንም መስቀሉ ወጣ።
ሦስት መስቀሎች ናቸው፤ ሁለቱ መስቀሎች ሽፍታዎቹ የተሰቀሉባቸው ሲሆኑ አንዱ የጌታችን ነው፤ ታዲያ እንዴት ለየችው ቢሉ የጌታችን መስቀል ታላላቅ ተዓምራትን አድርጓል ድውይ ፈውሷል ዓይ ነስውር አብርቷል።
ይህንን ቀን ቅድስት ቤተክርስቲያን "መስቀለ እየሱስ" ስትል ታከብረዋለች፤ በዛሬዋ ቀን ዝማሬው፤
ምስጋናው፤ ትምህርቱ፤ ቅዳሴው ፤ ንባቡ ሁሉም መስቀልን የሚመለከቱ ናቸው።
♱ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት የእውነተኛው መስቀል ግኝት በመጋቢት ወር ነው ተብሎ ቢታመንም መስቀል ግን በዐቢይ ጾም ወቅት በዓል እንዳይከበር ወደ መስከረም ተወስዷል።
😇 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ መስቀል የሚጣፍጥ ነገር ተናገረ እንዲህ ሲል፤
“ ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።”
♱ Tonight and tomorrow we Ethiopian Orthodox Christians celebrate The Feast Day which marks the discovery of The True Cross of Jesus Christ.
The discovery of this revered relic within Christianity can be traced back to the fourth (4th) century when the mother of the Roman Emperor Constantine, Queen Helena received divine guidance to its location.
According to legend, Queen Helena, now canonized, had a dream. In the dream, she was told to make a bonfire from which the smoke would show her the location where the True Cross of Jesus was buried.
After doing as she was instructed and the bonfire lit, the smoke rose high up to the sky and returned to the ground, exactly where the Cross had been buried. Thus began the yearly celebration of the discovery.
According to the Ethiopian Orthodox Church, the discovery of the True Cross is traditionally believed to have been in March, but Meskel was moved to September to avoid holding a festival during Lent, and because the church commemorating the True Cross in Jerusalem was dedicated during September.
“But far be it from me to boast except in the cross of our Lord Jesus Christ, by which[a] the world has been crucified to me, and I to the world.”
♱ መስቀሉን ይዘን ተሸክመን እናት ኢትዮጵያን ከሉሲፈራውያኑ እና ጭፍሮቻቸው የሞትና ባርነት ቀንበር ቶሎ ነፃ እናውጣት!
♱ መስቀል ጋሻና ጦር ይዘህ ለመርዳት ተነሳ፣ መስቀል ሰይፍህን መዘህ የዘበቡኝን ከበባቸው! ♱
🔥 አለም ወደ ኑክሌር ጦርነት እየተንደረደረ ነው፤ እነሱ ኒውክሌር ሊያብላሉ ሲቆፍሩ እኛ እኮ ከተቆፈረበት በተዓምር የወጣ ግማደ መስቀሉን ይዘን ነበር ♱
የበዓል ስም ፤ በመስከረም ፲፯ ቀን የሚከበር ታላቅ በዓል ፤ የመስቀል ቅዳሴ ቤቱ።
ጌታ በሰቀለበት አምሳል ከንጨት ከብረት ከብር ከወርቅ ከንሓስ ከእብነ በረድ ከሌላም ማዕድን የተሠራ ቄሶች በእጃቸው የሚይዙት ክርስቲያኖች ባንገታቸው የሚያንጠለጥሉት ፤ ሴቶችም በቀሚሳቸው ላይ ያስጠልፋታል። (ያበባ መስቀል) ፤ ካበባ የተጐነጐነ እንቍጣጣሽ።
ግንባር ማማተቢያ ጣት የሚያርፍበት ፤ ወይም የመስቀል ምልክት ዕመት የሚደረግበት። እረኛው ላውሬ የወረወረው ደንጊያ አቶ እከሌን መስቀሉን አለው ።
የክርስቶስ መስቀል በኹለት ረዣዥም ዕንጨት እጅና እግሩ የተቸነከረበት ከራሱ እስከ እግሩ ወራጅ ግንድ ከቀኝ እጁ ወደ ግራ እጁ ከአግዳሚውም ግንድ ባራት ማዕዘን ተመሳቅሎ የሚታየው መስቀልኛ ዕንጨት።
ሐዋርያ መስቀል ትርፍ ነገር ትርፍ ቅርጽ የሌለው ልሙጥ መስቀል።
ሕማማተ መስቀል የክርስቶስ ልዩ ልዩ መከራው በጥፊ መመታቱ መታሠሩ መገረፉ ግንድ መሸከሙ ራቁቱን መሰቀሉ አክሊለ ሦክ የሾክ አክሊል በራሱ ላይ መቀዳጀቱ ይኸንን የመሳሰለ ልዩ ልዩ መከራው ሕማማተ መስቀል ይባላል።
ልዩ ልዩ መስቀል የመስቀል ዐይነት ኹኖ በልዩ ልዩ አቀራረጽ በልዩ ልዩ ሥራ ተሠርቶ የሚታየውን በየሥዕሉ ማሳየት።
ቀራንዮ መስቀል በቀራንዮ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዋነኛው የቀራንዮ መስቀል።
ቀርነ በግዕዝ መስቀል እንደ በግ ቀንድ ኹኖ በተሠራው መስቀል በመጽሐፍ ድጕሰት ላይ የሚታይ ቆለፍ ቆለፍ ያለ።
ትእምርተ መስቀል የመስቀል ምልክት ወይም መስቀልኛ።
ነገረ መስቀል የመስቀልን ነገር መነጋገር መሥራት ማሳየት።
ዕርባን ሥራ መስቀል ብሩ ወርቁ በልዩ ልዩ አቀራረጽና ንቅስ ተነቅሶ በሙሻ ዘርየሚሠራ ዕርባን ሥራ ንቅስ መስቀል።
ዕርፈ መስቀል ማንካ ቀሳውስት ለሚቆርቡ ምዕመናን ደሙን የሚያቀብሉበት ማንካ በቤተ ክርስቲያን የሚኖር ዕርፈ መስቀል ይባላል።
የመስቀል አበባ በዘመነ ጽጌ የሚፈነዳው አበባ እንደ መስቀል ቅርጽና መልክ ያለው የመስቀል አበባ ይባላል።
የመስቀል ዎፍ ጥቍር ሰማያዊ የምትመስል በመስከረም በመስቀል በዐል ብቅ የምትል ድንቢጥ የመስከረም ዎፍ ትባላለች።
የመስቀል ደመራ በመስከረም ፲፮ ቀን ለመስቀል ዋዜማ ሕዝብ ኹሉ ርጥብ ዕንጨትን እያመጣ የሚደምረው ደመራ።
የመስቀል ጥቢ የመስከረም መስቀል ዘመን መስቀል ከዋለ በኋላ መስቀል ጥቢ መባል (ሰቀለ ሰቀለ መስቀል ([ግዕዝ])።
የመስከረም መስቀል እሌኒ ንግሥት በመስከረም አስጀምራ ያስቆፈረችው በመስከረም ዐሥራ ሰባት ቀን የሚውለው በዐል ነው።
የመጋቢት መስቀል በመጋቢት ዐሥር ቀን የሚውለው የመስቀል በዐል ነው።
የሰሎሞን መስቀል የሰሎሞን የሊሻኑ ዐይነት መስቀል።
የስቅለት ማግስት ከስቅለት በማግስት የሚውለው ቅዳሜ ሹር።
የስቅለት ዕለት ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል።
የተመሰቃቀለ መንገድ ዐራት ወገን ዐምስት ወገን ስድስት ወገን የሚያስኬድ አቋራጭ መንገድ።
የዐላማ መስቀል ለሃይማኖት ምልክት በዐላማ ላይ ለሚሰፋ የመስቀል ምልክት ወይም በሰንደቁ ላይ የሚታየው የዐላማ መስቀል።
የአንገት መስቀል እንደ ዕርባን ሥራ ወይም ልዩ ልዩ ሥራ ኹኖ ለአንገት እንዳይከብድ ትንሽ ኹኖ የሚሠራ መስቀል።
የዐጤ መስቀል በመስከረም ዐሥር ቀን ካህናት በቤተ መንግሥት ተሰብስበው ርእዩ ዘገብረ እግዚእነን ... አመልጥነው ተቀጸል ጽጌ እገሌ ሐፄጌ (ኅይለ ሥላሴ ሐፄጌ) እያሉ ወይም በእየ ጊዜው የነገሠዉን ንጉሥ የሚያወድሱበት ቀን ያጤ መስቀል ይባላል።
የእጅ መስቀል ጳጳሳት ኤጲስ ቆጶሳት ቀሳውስት በእጃቸው አዘውትረው የሚይዙት መስቀል።
ፀዋትወ መስቀል ([ግዕዝ]) ከመስቀል ወገን የኾነ መከራ ወይም የተቀደሱ የመስቀል ዕቆች።