Showing posts with label ቅዱስማርቆስ. Show all posts
Showing posts with label ቅዱስማርቆስ. Show all posts

Wednesday, September 10, 2025

እንኳን ለዘመነ ማርቆስ፣ ፍርድ ለሚሰጥበት እና ፍትሕ ለሚገኝበት አዲስ ፳፻፲፰/ 2018 ዓመት አደረሰን!

[፩ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕራፍ ፭]

እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤

በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤

ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤

የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።

እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።

እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤

እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።

በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤

በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።

በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁምል ያበረታችሁማል።

፲፩ ለእርሱ ክብርና ኃይል እስከዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።

፲፪ እየመከርኋችሁና የምትቆሙባት ጸጋ እውነትኛ የእግዚአብሔር ጸጋ እንድትሆን እየመሰከርሁላችሁ፥ የታመነ ወንድም እንደ ሆነ በቈጠርሁት በስልዋኖስ እጅ በአጭሩ ጽፌላችኋለሁ።

፲፫ ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

፲፬ በፍቅር አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። በክርስቶስ ላላችሁ ለሁላችሁ ሰላም ይሁን። አሜን።

😇 ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስን ያስገኘች ጽዮናዊቷ ኢትዮጵያ ናት | ፴ ሚያዝያ ቅዱስ ማርቆስ | ፻ኛ ዓመት


https://wp.me/piMJL-eXl

😇 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለም ላይ ካሰማራቸው ሐዋርያት መካከል ሐዋርያው ማርቆስ አንዱ ነው።

ሐዋርያው ማርቆስን በሚመለከት መሪራስ አማን በላይ “ሐዋርያው ማርቆስ ዜግነቱ ሮማያዊ ሲሆን፡ ትውልዱ ኢትዮጵያዊ ነው። በዚያን ጊዜ ግብጾች ቦታ አልነበራቸውም ሲሉ ተናግረዋል። ሐዋርያው ማርቆስ ቤተሰቦቹ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ነዋሪነታቸው ግብጽና ኢየሩሳሌም እንደነበረ በታሪክ ተጠቅሷል።

አባ ተስፋ ሞገስ፡ ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የይሑዳ አንበሳ ነው ሲሉ መጽሐፍ ጽፈዋል። ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የይሑዳ አንበሳ ነው የተባለው መጽሐፍ ገጽ 100 ላይ “ማርቆስ ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊ ነው” ሲሉ ጽፈዋል። እኒህ አባት ሐዋርያው ማርቆስን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሐዋርያት ኢትዮጵያዊ ደም ያላቸው መሆናቸውን በማመለከት ከፍ ተብሎ በተጠቀሰው መጽሐፍ ገጽ 42 ላይ፡ “ከኢትዮጵያውያን ዘር የሚወለደው ፊልጶስም ነው” ሲሉ ሁለቱ ሐዋርያት ከጌታችን ጋር ያደረጉትን የቃላት ልውውጥ በሚመለከት ጽፈዋል።

ከዚህ ላይ ማየት ያለብን እነዚህ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ቀድሞ ጀምረው ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉና ለክብር የማይሮጡ በመሆናቸው ማንነታቸው ሊታወቅ አልቻለም። እንኳን ቀድሞ በቅርቡ የዳ/ዊ አጤ ቴዎድሮስን ታሪክ የፃፉት አንዱ ደራሲ መጽሐፉን የዘመኑ የታሪክ ሊቃውንቶችን ጥቅስ ለመውሰድ ሲሉ “የማይታወቀው ደራሲ” እንደጻፈው እየተባለ ነው የሚጠቀሰው። የጥንት ኢትዮጵያውያን “እወቁልን” የማይሉ በመሆናቸው ብዙ የታሪክ አባቶቻችን ስምና ታሪክ ተደብቆ ቀርቷል። በዚህ ባለንበት አገር አሉ ከሚባሉት ሊቆች መካከል ለአንዱ የሊቀ–ጠበብት ማዕረግ ዩኒቨርስቲው ሲሰጣቸው አስተዳዳሪው ለተሰብሳቢው እንግዳ እንዲህ ብለው ነበር፦

ኢትዮጵያውያን ይህን ሰርተናል የማይሉ በስራቸው እንጂ ለወረቀት የማይጓጉ በመሆናቸው ይህ ዶ/ር እገሌ እንደሌሎች ዶክተሮች ማመልከቻ ይዞ ወደ ጽሕፈት ቤቱ መጥቶ አስቸግሮኝ አያውቅም። የስራውን ጥራትና ብቃት ዩኒቨርስቲው በማየቱ የሌቀ–ጠበብት ማዕረግ ሰጥቶታል” ብለዋል።

ትቤ አክሱም ገጽ 67 “ቅዱስ ማርቆስም ያባቱን ሀገር አስቀድሞም ያውቀው ስለነበረ መጥቶ እንዳስተማረ” ሲሉ ጽፈዋል። ከዚህ ላይ የኢትዮጵያውያን ከቀድሞ ጀምሮ የመጣው ታሪክ የሚያመለክተው ለክርስትና ሐይማኖት ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረጋቸውን ነው። ሐዋርያው ማርቆስን የመሰለ መምሕር ያስገኘች ኢትዮጵያ ናት። ላይ እንደተጠቀሰው ዛሬ ድረስ በህይወት ያሉ ደራሲያን ኮሎኔልነታቸውን፣ ጠበብትነታቸውን ወይም ሊቅነታቸውን ሳይጠቅሱ መጽሐፍ የጻፉ ደራሲያን ነበሩ። ምክኒያቱም ኢትዮጵያውያን አብዛኛው እወቁኝ የማይሉ ናቸው። በዚህ ምክንያት ከቀድሞ ጀምሮ ተያይዞ በመምጣቱ ሐዋርያው ማርቆስ ኢትዮጵያዊ መሆኑ ሳይታወቅ ኖሮ ነበር።

መሪራስ አማን በላይ፡ “ጉግሣ” መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 3 መጋቢት 1993 .. ገጽ 17 ላይ “የማርቆስን አክስት ማለት የበርናባስንና የአርስጦሎስን እህት ጴጥሮስን አግብቶ ነበር። እንዲሁሙ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የቤተ እስራኤል የሌዊና የይሑዳ ነገድ የሆነ ወደ ቀሬና ቀራኒዮ ወደ ቤተ መቅደስ ሊሰግድ መጥቶ ስሙም ስምዖን ይባል ነበር። በበነጋታው ከአባቱና ከናቱ ዘመድ ከስምዖን ጋር ማርቆስ የጌታችንን የክርስቶስን ግርፋትና ሕማማቱን እየተከተለ ተምልክቷል። አጎቱንም የአባቱን ዘመድ ኢትዮጵያዊ ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው የጌታን መስቀል እንዲሸከም አይሑዳ ሊያስገድዱት አይቷል ተመልክቷል” ሲሉ ጽፈዋል። ስምዖን ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥበት ምክንያት ስምዖን ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥበት ምክንያት ስምዖን ጥቁር መሆኑን በሌሎችም ታሪክ ታውቋል።

ሐዋርያው ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ስለሆነና ታሪኩን ስላወቁ ቀዳማዊ አጤ ኃይለ አጽሙ አጽሙ ቬነስ ግዛት / ከተማ ከሚቀር ግብጽ መግባት ይኖርበታል ብለው ከቬነስ መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን ጋር ያደረጉት ጥረት ቀላል አይደለም። ቀደም ሲል ግብጾች ሊያስመልሱ ያልቻሉትን አጤ ኃይለ በጥረታቸው የቅዱስ ሐዋርያው ማርቆስ አጽም ወደ አፍሪቃዋ ግብጽ እንዲገባ ሆነ። ይህ ታሪክ በመሆኑ ሊገለጽ የሚገባው ሲሆን፡ ጃንሆይ መሠረት ያደረጉት ዋናው ነጥብ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ በዘሩ ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ነው።

የአጤ ኃይለ ታሪክ” ከሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 1132 ላይ “ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ ወደ ግብጽ ገብቶ ክርስትናን በማስተማር ላይ እያለ የክርስቲያኖችን ዕምነት የሚጠሉና በጣዖት የሚያመልኩ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ለምደውት ለቆየው አምላካቸው በጣም ቀናኢ የሆኑ በአሌክሳንድርያ መንገድ ላይ እየጎተቱ አሰቃይተው ገደሉት። እንደሞተም አሌክሰንድርያ በሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ቀበሩት። በዚህ ቦታ ተቀብሮ ለብዙ ዘመን ከቆየ በኋላ በ820 .ም ሁለት የቬኑስ ነጋድያን አጽሙን በድብቅ ከተቀበረበት አስወጥተው ወደ ቬነስ ነጋድያን አጽሙን በድብቃ ከተቀበረበት አስወጥተው ወደ ቬነስ ወሰዱት በዚህ ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን አኑረውት ቦታው የበላይ ቅዱስ ሆኖ በክብር ይኖር ነበር። ስለሆነም የግብጽ ቤተ ክርስቲያን እንዲሰጣት በየጊዜው ከመጠየቅ አልቦዘነችም ነበር። ግርማዊ ንጉሠ ነገሥታት ቀዳማዊ ኃይለ ም ለግብጽ እንዲመለስ ብዙ ጊዜ ጠይቀዋል።

ነገር ግን ሁሉም የሚፈጸመው እግዚአብሔር በፈቀደው ጊዜ ስለሆነ ጊዜው ሲደርስ የሮማው ርዕሠ ሌቀ ጳጳስ ጳውሎስ 6ኛ ስለፈቀዱ በሞተ በ1900 በተወሰደ 1140 ዓመት ወደ ጥንተ ቦታው ለመመለስ በቃ።” ካለ በኋላ አጽሙ የገባበትን ቀን ሲገልጹና ጃንሆይም በስፍራው መኖራቸውን ሲያብራሩ ገጽ 1133 ላይ፡ “የቅዱስ ማርቆስ አጽም ከቬነስ ወደ ግብጽ የገባው ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት በአለበት ሰኔ 17 ቀን 1960 .ም ነው።” ብለዋል።

የሐዋርያው ማርቆስ አጽም ግብጻውያን ራሳቸው ካልሸጡት አልያም ጠቋሚ ካልሆኑ ቁጥራቸው ትንሽ በሆነ ነጋዴዎች ተሰርቆ ሊወሰድ አይችልም። መሠረቱን ካወቁ ጀምሮ አጽሙን ለማስመለስ ብዙ ሙከራ ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም ነበር። በዚህ ምክንያት የሐዋርያው ማርቆስን አጽም ለማስመለስ የቻሉት ኢትዮጵያዊው ቀዳማዊ አጤ ኃይለ ናቸው። ያም በመጀመሪያ ጌታ ሲወለድ የእጅ መንሻ የሰጡ ሰብዓ ሰገል ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ኋላም ጌታችን በስደት መጥቶ የኖረባት ስትሆን ተመልሶም መጥቶ ወንጌልን ያስተማረባት አገር ናት። ከዚያም በጅሮንድ ጃንደረባ ባኮስ በ34 .ም ተጠምቆ ተመልሶ ወንግጌልን ያስተማረባት ኢትዮጵያ አገራችን ናት።

🛑 September 11: A Conspiracy Against Jesus, The Virgin Mary & Ethiopia?

https://rumble.com/v5ejhyc-september-11-a-conspiracy-against-jesus-the-virgin-mary-and-ethiopia.html

https://wp.me/piMJL-dCQ

https://www.bitchute.com/video/xuv8IMWDclHs

Was Jesus Born on 9/11?

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስከረም ፩ ነውን የተወለደው?

Vigil Held for 3 Ethiopian Christians Killed in Mount Washington, Ohio Shooting

https://www.bitchute.com/video/5VS5gtICgXDP/ https://rumble.com/v6yuwj6-vigil-held-for-3-ethiopian-christians-killed-in-mount-washington-oh...