Showing posts with label Bees. Show all posts
Showing posts with label Bees. Show all posts

Friday, November 21, 2025

ህመምተኞች በንቡ የሚፈውሱበት ተዓምረኛው "ንቡ ቅዱስ ሚካኤል" ቤተ ክርስቲያን

በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ላይ ጠላቶቿ የዘር ማጥፋት ጂሃድ ከመክፈታቸው በፊት…

🐝 “ንቡ ሚካኤል” በአዲስ አበባ፡ 'አያት' የሚባለውን ቦታ አለፍ ብሎ በሻሌ ኮረብታ ላይ የሚገኝ ቤተክርስቲያን ነው። ወደዚህ ቤተክርስቲያን እንዴት እነደመጣሁ ሁሉ አላውቅም፤ ቅዱስ ሚካኤል ነው ያመጣኝ።

የንቡ ቀፎ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ነው ያለው። የንቡም መንጋ ቤተልሔም ውስጥ ገብቶ እስከአሁን ድረስ ሰፍሮ ይገኛል። በቅዳሴ ሰዓትና ታቦት በሚወጣበትም ጊዜ ሁሉ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ንቡ ይወጣል። በንብ የሚነደፍ ከተለያዩ በሽታዎች ይፈወሳል። ንቦቹ ዝም ብለው አይናድፉም፤ የተፈቀደለት ሰው ነው ሊነደፍ የሚችለው። ይሄን እንደሰማሁ በጣም ተደስቼ "ጢናማ ያደረገኝ ቸሩ እግዚአብሔር ይመስገን፤ ዶክተር ካየሁ ሃያ ዓመት ገደማ ሆኖኛል ፥ ግን ሳጥናኤል አገር እየተኖረ ጋኔን መግቢያ ቀዳዳ አያጣምና በቃ ንቦቹ በውስጤ ሊኖር የሚችለውን መርዝ ነቅለው ሊያወጡልኝ ነው ብዬ ቤተክርስቲይኑን መዞር እንደጀመርኩ ከየት እንደመጣ ያላየሁት አንድ ጎረመሳ ልጅ አብሮኝ ይዞር ጀመር(አልፎ አልፎ ቪዲዮው ላይ ይሰማል)“ከየት መጣህ? ትምህርት ቤት የለህም እንዴ? እንዴት ወደዚህ ብዙ ሰው ወደ ሌለበት ቦታ መጣህ?" ብዬ ጠየቅኩት። እርሱም፡ "አይ መንገድ ላይ ከጓደኞቼ ጋር በመኪና መጥተን ተጠፋፋን፣ ከዚያም እኔ ዝም ብዬ ወደዚህ መጣሁ" አለኝ። ትህትና ያለው ስለነበር አመንኩት። ንቦቹ ቢነድፉኝ በማለት ቤተክርስቲያኑን መዞሩን ቀጠልኩ ግን አሁንም አብሮኝ ይዞራል። በቃ ስላልተነደፍኩ ራመድ ብዬ ከአንዲት ሱባኤ ከያዙና ደስ ከሚሉ እናት ጋር ማውራት ጀመርኩ። ስለቤተክርስቲያኑ በይበልጥ ማወቅ ከፈለግክ በጥቅምት ተመልሰህ ና፤ ያኔም ማር ይቆረጣል ፈውስ ነው ይዘህ ትሄዳለህ አሉኝ። እኔም ከምስጋና ጋር በጥቅምት ስለምጓዝ እንደማልችል አሳውቂያቸውና ተሰናብቻቸው ድንቅ የሆነ ቦታ ላይ ካለው የቤተክርስቲያን ግቢ ወጣሁ። አሁንም ያ ጎረምሳ ተከትሎኝ መጣ፤ "እስኪ ባክህ ወደ አያት የሚወሰደው ታክሲ የሚቆምበትን ቦታ አሳየኝ" አልኩት፤ " ቦታውን ካሳየኝ በኋል ሞባይሉን አውጥቶ መደወል ጀመረ። መንገዱ በጣም ጭር ያለ ነው፣ መኪናም ብዙ የለም። በዚህ ጊዜ ከአውቶብስ ማቆሚያው ፊት ለፊት አንድ የስልክ ምሰሶ ላይ ነጭና ጥቁር ቀለም ያለው ቁራ ወደ እኛ አቅጣጫ ሲጮህ ይሰማል። በጣም የሚገርም ነው፤ "ጉሮሮው እስኪወጣ" ድርስ በኃይል ነበር የሚጮኸው። "ምን እያለን ይሆን?” አልኩት ለልጁ፡ በዚህ ሰዓት መልስ ሳይሰጠኝ ፊቱ ሲለዋወጥ አየሁት። በዚህ ጊዘ አንድ ታክሲ ከች አለ። እንደገባሁ ታክሲው በቅዱስ ሚካኤል እና ቅዱስ ገብርኤል ስዕሎች የደመቀ ነበር። "ዋው! ቅዱስ ሚካኤል በቁራው በኩል ስለሆነ ነገር እያስጠነቀቀኝ ነበር" አልኩ፤ በጣም በመገረምና በመደሰት።

ከሁለት ቀን በኋላ፡ ማታ ላይ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን አካባቢ ሦስት ቻይናዎች ወደ ዘረጓቸው እጆቻቸው ሞባይላቸውን አብርተው አየሁና "እንግሊዝኛ ትችሉ ይሆን ምን ችግር ገጠማችሁ?” አልኳቸው። እነርሱም በጠራ እንግሊዝኛ "እጃችንን ቢንቢዎችን ልናስነክስ ፈልገን ነው፤ ቢንቢዎች ጎጂ ባክቴሪያዎችን ያጠፉልናል፤ እዚህ አገር አየሩ ቆንጆ ስለሆነ ጤናማ ቢንቢዎች ናቸው" አሉኝ። ቻይኖቹ ትክክል ናቸው፤ በቅድስት ኢትዮጵያ ንቦቹና ቢንቢዎቹ መድኃኒቶቻችን ናቸው፣ አዕዋፋቱና እንስሳቱ ረዳቶቻችን ናቸው። ቸሩ እግዚአብሔር ለሕዝባችን ሁሉንም ነገር በነፃ አዘጋጅቶለት ሳለ፡ ከወጣት እስከ አዛውንቱ ለቀላል በሽታ የፈረንጁን ኪኒንና መርፌ በውድ ገንዘብ ሲሸምት ሳይ በጣም አዝናለሁ።

በአውሬው መዳፍ ሥር የሚሰቃዩትን ወገኖቻችንን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በዕለተ ቀኑ ይድረስላቸዉ ካሉበት መከራና ስቃይ በምልጃው ያውጣቸው! የእግዚአብሔርን ሕዝብ ከመከራ ታዳጊ ቅዱስ ሚካኤል ነውና የሃገራችን ጠባቂ የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ረድኤት በረከቱ ከሁላችን አይለየን!!!

ተ ዓምረኛው በሻሌ ንቡ ቅ/ሚካኤል እና ሰማዕቱ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን

የእግዚአብሔርን ሥራ በምድር ያደረገውን ታምራት እንድታዩ ኑ” (መዝ. ፵፭፥፰)

🐝 በንብ መንጋ የተከበበው የበሻሌ(ንቡ) /ሚካኤል፣ ቅ/እስጢፋኖስ እና ወአባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ቤተክርስቲያን አመሰራረትና ገቢረ ተዓምራት አጭር መግለጫ፤

ቤተክርስቲያኑ ከመመስረቱ በፊት በቦታው ላይ ሲከናወኑ የነበሩ ልዩ ልዩ ተዓምራት፡-

. ለብዙ ዓመታት ከተለያየ ቦታ ተጣልተው የነበሩ ምዕመናን ቦታው ላይ እየመጡ እርቀ ሰላም ሲፈጽሙበት ኖረዋል፤

. ቤተክርስቲያኑ ከተተከለበት ቦታ ትልቅ የጽድ ዛፍ ላይ የሚወጣው ሙጫ እንደ እጣን ጢስ ሽታ ለብዙ ዓመታት አካባቢውን መዓዛው (ሽታው) ያውድ ነበር፡፡

. በዚሁ ቦታ ላይ ሌሊት ሌሊት የመላዕክት ዝማሬ (ጣዕመ ዜማ) የከበሮ ድምጽ ይሰማ እንደነበረ በዕድሜ የገፉ የአካባቢው አዛውንቶች ተናግረዋል፡፡

. በአካባቢው ከሚኖሩ ምዕመናን መካከል በመልካም ስራቸው የታወቁና ከዘጠና/90 ዓመት በላይ ዕድሜ የነበራቸው እናት የቅዱስ ሚካኤል ታቦት(ጽላት) እንደሚተከል በተደጋጋሚ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ይናገሩ ነበር፡፡

. ቀደም ሲል በእነ አብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት አካባቢ ጀምሮ ከተለያየ አካባቢ የሞቱ አባቶች አስከሬናቸው እየመጣ ሥርዓተ ቀብር ሲፈጸምበት የቆየ እና በተለያየ ጊዜ የቀስተ ደመና ብርሃን በመቃብሩ ላይ ይታይ እንደነበር በአካባቢው የሚኖሩ በዕድሜ የገፉ አዛውንቶች በግልጽ መስክረዋል፡፡ ዛሬም መቃብሩ በግልጽ ይታያል፡፡ ይህ ሁሉ ታሪክ ሲከናወን ከቆየ በኋላ እግዚአብሔር የፈቀደው ጊዜ ሲደርስ በአካባቢው ከሚኖሩ በዕድሜ ከገፉ አዛውንቶች መካከል በአንድ አርሶ አደር ምዕመን አማካኝነት በእግዚአብሔር ፈቃድ በተደጋጋሚ ራዕይ ተገልጾላቸው ያርሱበት የነበረውን ይዞታቸውን መሬት ለዚህ ታቦት መትከያ ቤተክርስቲያን እንዲሰራ መሬት በመስጠት አሁን በሚገኘው መቃኞ ቤተክርስቲያን ግንቦት 12 ቀን 2001 .ም ታቦቱ ሊገባ ችሏል፡፡

በቤተመቅደሱ ስለሚገኘው የንብ መንጋ አገባብ (አመጣጥ)

😇 እግዚአብሔር አስቀድሞ ቦታውን ስለመረጠው፡-

. ሕዳር ፲፪/12 ቀን ፳፻፪/2002 .ም የቅዱስ ሚካኤል በዓል ሲከበር በዋዜማው ሊቃውንቱ በአገልግሎት ላይ እንዳሉ ማለትም ሕዳር ፲፩/11 ቀን ፳፻፪/2002 .ም ከቀኑ 900 ሰዓት ገደማ ከምስራቅ አቅጣጫ የንብ መንጋ መጥቶ የቃል ኪዳኑ ታቦት በሚገኝበት በመንበሩ ውስጥ ገብቶ ካደረ በኋላ በነጋታው ታቦቱ ወጥቶ በሚከበረበት ጊዜ ንቡ ከመንበሩ ወጥቶ እንደ ደመና ረቦ ካሉት ምዕመናን ጋር ታቦቱን ዙሮ አክብሯል፡፡ በዕለቱም ይህን አስደናቂ ታምር ያዩና የተመለከቱ ምዕመናንም በከፍተኛ ድምጽ እግዚአብሔርን አመስግነዋል፡፡

. ሕዳር ፲፩ /11ቀን ፳፻፬/2004 .ም የድንግል ማርያም ዕለት ካህናቱ ቅዳሴ ገብተው በሚቀድሱበት ጊዜ ቅዱስ ወንጌል ሲነበብ የንብ መንጋ መጥቶ ከቤተክርስቲያኑ ጉልላት ላይ የመስቀል ምልክት ሰርቶ ከሰፈረ በኋላ ከቀኑ አስራ አድን/1100 ሰዓት ላይ ተነስቶ ቤተክርስቲያኑን ዙሮ ወደ ቤተልሔም ውስጥ ገብቶ እስከአሁን ድረስ ሰፍሮ ይገኛል፡፡

. ታህሳስ ፱/9 ቀን ፳፻፬/ 2004 .ም ከቀኑ ዘጠኝ/900 ሰዓት የንብ መንጋ መጥቶ ከቤተክርስቲያኑ ጎን ላይ ከሰፈረ በኋላ ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ተኩል/ 1130 ተነስቶ ቤተክርስቲያኑን ዙሮ ወደ ግብር ቤት ገብቶ እስከአሁን

ድረስ ሰፍሮ ይገኛል፡፡

. ታህሳስ ፲፱/19 ቀን ፳፻፭/2005 .ም የቅዱስ ገብርኤል ዕለት ካህናት ቅዳሴ ገብተው በሚቀድሱበት ጊዜ ቅዱስ ወንጌል ሲነበብ የንብ መንጋ መጥቶ በሴቶች መግቢያ በር ወደቤተክርስቲያኑ ከገባ በኋላ በቀጥታ ወደ ቤተመቅደሱ ውስጥ ገብቶ በአጎበሩ ላይ ሰፍሯል፡፡ ይህ በቤተክርስቲያናችን ላይ ያለው የንብ መንጋ ማሩ ተቆርጦ በተለያየ ጊዜ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ተሰጥቶ ከአገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ በጉበት፣ በካንሰር፣ በኪንታሮት፣ በስኳር፣ በአስም፣ በጨጓራ፣ በኩላሊት፣ በደም ግፊት፣ በኤች አይ ቪ፣ ሽባዎች፣ አይነስውራን፣ አፈ ዲዳዎወች፣ መስማት የተሳናቸው፣ በጭንቀትና በልዩ ልዩ በሽታ የታመሙ ሰዎች ማሩን በልተው ጸበሉን ጠጥተው እምነቱን ተቀብተው ከበሽታቸው ተፈውሰው ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ እንዲሁም ለብዙ ዓመታት ልጅ አጥተው የነበሩ ሰዎች (መካኖች) በአንድ ጊዜ ሁለት ልጆች መንታ እንዲሁም በአንድ ጊዜ ሶስት ልጆች መንታ ወልደው

ታቅፈው መጥተው ጥምቀተ ክርስትናቸውን በዚሁ ቤተክርስቲያን እንዲፈፀም ማድረጋቸውና ሌሎች በዚህ አነስተኛ ጽሁፍ ሊገለፁ የማይችሉ በርካታ ገቢረ ተዓምራትና ፈውሶች እስከአሁኗ ሰዓት እየተደረጉ ናቸው፡፡

ክብርና ምስጋና ለአምላካችን ለልዑል እግዚአብሔር ይሁን አሜን፡፡

😇 በእግዚአብሔር ፈቃድ በንቦቹ የተደረጉት ተዓምራት በከፊል

. ሕዳር ፲፪/12 ቀን ፳፻፪/2002 .ም የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል ታቦቱ ወጥቶ በሚከበርበት ጊዜ ከቤተመቅደሱ ያለው ንብ ወጥቶ ታቦቱን አክብሯል፡፡

. ፳፻፫/2003 .ም የስቅለት በዓል ሲከበር ንሴብሆ እየተባለ በሚዘምርበት ጊዜ ንቡ ወጥቶ ቤተክርስቲያኑን ዙሮ ገብቷል፡፡

. መጋቢት ፲፪/12 ቀን ፳፻፬/2004 .ም የቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ በዓል ቅዳሴ እየተቀደሰ ሳለ የቤተመቅደሱ ንብ ከመንበሩ ላይ የመስቀል ምልክት ሰርቶ (ሰፍሮ) ታይቷል፡፡

. ሕዳር ፲፩/11 ቀን ፳፻፭/2005 .ም ንቡ ለመጀመሪያ ጊዜ የገባበትን ዕለት ለማስታወስ ከቀኑ 400 ሰዓት ላይ ንቡ ወጥቶ ቤተክርስቲያኑን ዙሮ ገብቷል፡፡

. ፳፻፭/2005 .ም ፀሎተ ሐሙስ የሕጽበተ እግር ጸሎት ሲከናወን የመቅደሱ ንብ ወጥቶ ፀበሉ ላይ ሰፍሮ (ረቦ)ታይቷል፡፡

. ፳፻፮/2006 .ም እሁድ የሆሳዕና በዓል ሲከበር ሆሳዕና በአርያም እየተባለ እየተዘመረ ዑደት በሚደረግበት ጊዜ ብዙ ምዕመናን ባለቡት የቤተመቅደሱ ንብ ወጥቶ ዞሮ ገብቷል፡፡ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል፡፡ ለዘላለሙ አሜን፡፡

📦 በቤተክርስቲያኑ ላይ የቃል ኪዳኑ ታቦት የሚነግስበት ቀናት፤

. ሕዳር ፲፪/12፣ ጥር 12፣ ግንቦት 12 ቅዳሴ ቤቱ፣ ሰኔ 12 ቀን የመልዓኩ የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በየዓመቱ ታቦቱ ወጥቶ ይነግሳል፡፡

. ጥቅምት ፲፯/17 እና ጥር ፩/1 ቀን የሰማዕቱ የቅዱስ እስጢፋኖስ ዓመታዊ በዓል ታቦቱ ወጥቶ ይነግሳል፡፡

. ታሕሳስ ፲፰/18 እና ሐምሌ ፳፮/26 ቀን የጻድቁ አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ዓመታዊ በዓል ታቦቱ ወጥቶ ይነግሳል፡፡ በእነዚህ የንግስ በዓላት ላይ ከቤተመቅደሱ የተቆረጠው ማር ለመድኃኒትነት ይሰጣል፡፡

😇 የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት፣ የቅዱስ እስጢፋኖስ እና የጻድቁ አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን ፡፡

😇 የገናናው መልአክ የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃው አይለየን፣ በጸሎቱ ይማረን።

Leftists + Islamists + Protestants are Waging a Genocidal Jihad on Ancient Christians of Ethiopia

https://rumble.com/v72pt2k-leftists-islamists-protestants-are-waging-a-genocidal-jihad-on-ancient-chri.html https://www.bitchute.com/video/g...