https://www.bitchute.com/video/wj3ezXqHgO8d/
😇 እንኳን ለሊቀ መልአኩ ለቅዱስ ኡራኤል ዓመታዊ በዓል አደረሰን!
❖ ገብርኤል 🧕 ማርያም 😇 ኡራኤል ❖ ጊዮርጊስ ❖ ተክለ ሐይማኖት ❖ መርቆርዮስ ❖ ዮሴፍ ❖ መድኃኔ ዓለም
በመላእክት ከተማ በራማ ካሉት ሦስት ነገዶች ዉስጥ አንዱ ነገድ ሥልጣናት ይባላል፡፡ በሥልጣናት ላይ ከተሾሙ ሊቃነ መላእክት ዉስጥ አንዱ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሱርያል ይባላል፡፡ ሱርያል የሚለዉ ስም በአንዳንድ ድርሳናት ካልሆነ በስተቀር እምብዛም አይታወቅም ትርጉሙም ‹ዐለቴ እግዚአብሔር ነዉ›ማለት ነዉ፡፡ ሱርያል የቅዱስ ዑራኤል ሌላ ስሙ ነዉ፡፡ ዑራኤል ማለት ‹እግዚአብሔር ብርሃን ነዉ›ማለት ነዉ፡፡ በቤተ ክርስቲያንም በስፋት የሚተወቀዉ ስም ዑራኤል የሚለዉ ስም ነዉ፡፡/ድርሳነ ዑራኤል ፲፱፻፺፩/1991 ገጽ ፲፬/14/ በመጽሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ስለ ቅዱስ ዑራኤል በስፋት የምናገኘዉ በመጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ነዉ።
ዕዝራን ይራዳዉ የነበረ ፤ለዕዝራም ጠፍተው የነበሩ የብሉይ ኪዳን መጻህፍትን እንደ ገና እንዲጽፋቸዉ ጽዋ ልቦና አጠጥቶ ምሥጢር የገለጠ ቅዱስ ዑራኤል ነዉ፡፡(ዕዝ ሱቱ፪ )።
‹በመብረቅና በነጎድጓድም ላይ የተሾመ ታላቅ መላክ ነዉ›(ሔኖክ ፮፥፪)
ምሥጢረ ሰማይም ለሔኖክ ያሳየዉ ዕዉቀትን የገለጠለት እርሱ ቅዱስ ዑራኤል መሆኑን ጽፏል። (ሔኖክ ፳፰፥፲፫፡፲፬)።
እመቤታችንም በኪደተ እግርዋ ኢትዮጵያን በዞረች ጊዜ ቅዱስ ዑራኤል ያገለግላት እንደነበርና እንዳስጎበኛትም በድርሳነ ዑራኤል ተጽፏል።
ለአዳም የድህነትን ዜና የነገረዉ ቅዱስ ዑራኤል ነዉ ዮሴፍን ብርታት ሰጥቶ ከብእሲት ጲጥፋራ ያዳነዉ ቅዱስ ዑራኤል ነዉ ለዕዝራ ምሥጢር የገለጠለት ቅዱስ ዑራኤል ነዉ የሚያረጋጋ ለኃጢያተኞች ምህረት የሚለምን መልአክ ነዉ። (ስንክሳር ጥር)።
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በሐይቅ እስጢፋኖስ ለገዳሙ መነኮሳት እህል እየፈጨ ዉሃ እየቀዳ እመቤታችንን እየተማጸነ ሲኖር አንድ ቀን ከሥዕሏ ሥር እየሰገደ ሳለ መልአኩ ዑራኤል ተገልጦ ጽዋህ ልቦና አጠጣዉ።ከዚያ ጀምሮ ምሥጢረ ሰማይ ወምድር ተገልጦለት ከ ፵/40 በላይ መጻሕፍትን ደርሷል። (መጽሐፈ አርጋኖን )።
በዕለተ ስቅለት የጌታ ደሙን በብርሃን ፅዋ ተቀብሎበዓለም የረጨ ቅዱስ ዑራኤል ነው። ሐምሌ ፳፩/21 እና ፳፪/22 ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበት ነው።
በአምላኩ አማላጅነቱን ኑና ተማጸኑት። በጸሎቱ ለተማጸነ ከአምላኩ በረከትን ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ እርሩህ መልአክ ነው። አሁንም ይህ ዓለም በአማላጅነቱ አምኖ ጸበሉን ቢጠጣ ከክፉ በሽታ እንደ
ሚፈወሱ ቃለ ኪዳን ተሰጥቶታል፣በፍጹም መጠበቅን ጠብቆ ለዚህ ያደረሰን አምላካችን ክብርና ምስጋን አምልኮትና ውዳሴ ይድረሰውና ይህን ታላቅ መልዕክ በችሎታችን መጠን እንድናመሰግን ና እንድናገለግል እግዚአብሔር ይርዳን አምላክ ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን፤ ከመልዐኩ ከቅዱስ ዑራኤል በረከት ረድኤት ያሳትፈን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
😇 Today, July 29, 2025, we Ethiopian Orthodox Tewahedo Christians celebrate the Annual Feast Days of The Archangel Saint Uriel
This story reveals a fascinating and hidden chapter from the crucifixion of Jesus that many aren't aware of. According to Ethiopian Orthodox tradition, angels Michael and Uriel played an essential role during the crucifixion, especially in the moment when Jesus' side was pierced. As His blood flowed, Uriel collected it in a divine chalice, and together with Michael, they carried it back to Ethiopia, sanctifying the land. This act not only marked Ethiopia as a holy land but also established a profound spiritual connection between the nation and Christ's sacrifice, a tradition that remains central to Ethiopian Orthodox Christianity today.
😇 ቅዱስ ዑራኤል / 𝐒𝐚𝐢𝐧𝐭 𝐔𝐫𝐢𝐞𝐥 𝐓𝐡𝐞 𝐀𝐫𝐜𝐡𝐚𝐧𝐠𝐞𝐥
Uriel means “God is my light”or “Light of God”. In the Ethiopian Homily on the Archangel Uriel, he is depicted as one of the great archangels who has interpreted prophecies to Enoch and Ezra, and the helper of both of them. According to the Ethiopian Homily, at the time of the Crucifixion of Iyesus (Jesus), Uriel dipped his wing in the blood and water flowing from Christ's flank and filled a cup with it. Carrying the cup, he and the Archangel Mikael (Michael) rushed into the world and sprinkled it all over Ethiopia, in every place where a drop of blood fell a church was built. Uriel is often depicted carrying a chalice filled with the blood of Christ in Orthodox Tewahedo iconography.
📖 𝐁𝐢𝐛𝐥𝐞 𝐕𝐞𝐫𝐬𝐞𝐬:
❖ 𝐄𝐧𝐨𝐜𝐡 9:1, 10:1, 19:1, 20:2, 21:5, 27:2, 33:4, 72:1, 74:2, 75:3-4, 78:10, 79:6, 80:1.
❖ 𝟐 𝐄𝐬𝐝𝐫𝐚𝐬 4:1, 5:20, 10:28.
The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church commemorates his feast on the 22nd of every month and his major feast days are Tiri 22 (January 30) and Hamle 22 (July 29).
😇 O Saint URIEL Archangel Fire of God, teach us to be patient, in order to fight the demon of anger, so that we may become, like Jesus, the patient lamb, to belong to his royal dynasty. Amen! Amen! Amen!
😇 The Temple of Archangel Uriel | የሊቀ መላእክት ዑራኤል ቤተ መቅደስ
😇 ቅዱስ ኡራኤል ኢትዮጵያን የቃል ኪዳን ሃገርሽ ብሎ ለጽዮን ማርያም ሰጥቷታል፤ መሬቱ የእግዚአብሔር እንጅ 'ኬኛ!' አይደለም
❖ አዲስ አበባ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን ፪ሺ፲፪ ዓ.ም
አህዛቡ እና አረማውያኑ እየተዋጉ ያሉት ከኢትዮጵያ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ነው
ኡራኤል የሚለው ስም `ኡር' እና 'ኤል' ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ኡራኤል ማለት ትርጉሙ “የብርሃን ጌታ”፣ ”የአምላክ ብርሃን" ማለት ነው። በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የተመሰረቱ ገዳማት በቅዱስ ኡራኤል መሪነት ነው።
የቅዱስ ኡራኤል ፀሎት በያለንበት ይድረስ!
😇 Archangel Uriel and the Accursed Valley (The Ethiopic Book of Enoch Explained)
https://www.bitchute.com/video/dlkVUzheCYjV/
😇 ቅዱስ ኡራኤል | መጽሐፈ ሔኖክ፤ የሊቀ መላእክት በቀል በአዛዝኤልና ጭፍሮቹ ላይ
ኮከብ እንደ ፀሐይ የራሷ ብርሃን አላት፤ ታበራለች ፥ ጨረቃ ግን ብርሃን ትሰርቃለች እንጅ የራሷ ብርሃን የላትም፣ ጨለማ ናት።
😇 ኡራኤል የሚለው ስም `ኡር' እና 'ኤል' ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ኡራኤል ማለት ትርጉሙ “የብርሃን ጌታ”፣ ”የአምላክ ብርሃን" ማለት ነው። በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የተመሰረቱ ገዳማት በቅዱስ ኡራኤል መሪነት ነው።
❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፱፡፩፥፪]❖
ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል። ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች።
😇 የሔኖክ ሰማይ ሰሌዳ በቅዱስ ኡራኤል ዕለት 😇
✞ሐሙስ ሐምሌ ፳፪/፪ሺ፲፫ ዓ.ም✞
😇 ኖኅ እንደ ሔኖክ ቅድመ አያቱ መላ ዘመኑን ከፈጣሪው ጋር በመጓዝ ስለ ፅድቁ ቅዱስ መፅሐፍ የመሰከረለት ሰው ነው። [ዘፍ ፮፥፱]
ቅዱስ ኡራኤል ምስጢረ ሰማይንና እውቀትንም ሁሉ ለሔኖክ እንደገለጸለት ሁሉ ለሔኖክ የልጅ ልጅ ለኖኅም በዚያ መከራ ቀን መርከብ ለመስራት በሚያዘጋጅበት ጊዜ ምክር በመለገስ ቁሳቁስ በማቅረብ ከመርከብም ከወጣ በኃላ በሽምግልናው ዘመን ቅዱስ ኡራኤል አልተለየውም ነበር።
❖ ኡራኤል የሚለው ስም `ኡር‘ እና ‘ኤል‘ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
❖ ኡር ማለት በእብራይስጥ ብርሃን ማለት ሲሆን ኤል–ማለት ደግሞ አምላክ ማለት ነው ።
❖ አንድ ላይ ሲነበብ –ኡራኤል ማለት የብርሃን አምላክ ወይም የብርሃን ጌታ ማለት ነው ።
ቅዱስ ኡራኤል ከ፯/7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ፣ ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልዓክ ነዉ። በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። [መጽሐፈ ሔኖክ ፮፥፪] ፣ ምስጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሔኖክ የገለጸለት የፀሀይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሔኖክ ነግሮታል። ፟[መጽሐፈ ሔኖክ ፳፰፥፲፫]
ለማንኛውም፡ ቀደም ያሉት ኢትዮጵያውያን አባቶች በዲያብሎስ ተታለው(የናግራን ክርስቲያኖች መስለዋቸው) የመጀመሪያዎቹን መሀመዳውያን መቀበላቸው ቀናተኛውን አምላካችንን እግዚአብሔርን አስቆጥተዋል። ሕዝቧ የራሱን እና የአምላኩን ጠላት ለይቶ በማየት ለመዋጋት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ላለፉት 1400 ዓመታት በጣም ብዙ መስዋዕቶችን ለመክፈል ተገድዷል። ምከረው ምከራው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው! እንዲሉ። ሆኖም በመላው ዓለም፡ በተለይ በኢትዮጵያ ሃገራችን ለውድቀቷ ካለሆነ በቀር ምንም ዓይነት በጎ ነገርና ይህ ነው የሚባል አዎንታዊ አስተዋጾ አበርክቶ የማያውቀውን እስልምናን ዛሬም ሌላ ብዙ ጥፋት ካስከተለ በኋላ ከእነ ሰይጣን ቤቱ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ምድር ቸሩ እግዚአብሔር በእሳት ይጠርገዋል። በዚህ 100% እርግጠኛ ነኝ!
የቅዱስ ኡራኤል ፀሎት በያለንበት ይድረስ!
❖❖❖ቅዱስ ኡራኤል ኢትዮጵያን የጽዮንን ልጆችን አደራ፤ በእሳት ሰረገላ በነበልባል ታጅበህ ለተልዕኮ የምትፋጠን የአምላካችን አገልጋይ ወራዙተ ኢትዮጵያን በብርሐናዊ ክንፍህ ሸፍነህ ከመርዘኞች የሞት ቀስት ከቀሳፊ ነገር ሁሉ ሰውረን!❖❖❖
❖ ❖ ❖ ድርሳነ ኡራኤል ❖ ❖ ❖
ምድረ ኢትዮጵያ ፦ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሴፍና ሰሎሜ በደመና ተጭነው ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ናግራን ከተባለ ሀገር ደረሱ። በናግራን ሳሉ ጌታ እንዲህ አለ። ከቀኝ ጎኔ የሚፈሰው ደሜ በብርሃናት አለቃ በዑራኤል እጅ ተቀድቶ በቅድሚያ በዚች ሀገር ይፈሳል ወይም ይረጫል። እናቱንም እንዲህ አላት አንቺ በድንግልና ጸንሰሽ በድንግልና እንደወለድሽኝ አምነው የሚያከብሩሽ በእኔም የሚያምኑ ብዙ የተቀደሱ ሰዎች በዚህ ሀገር ይወለዳሉ። ከናግራን ተነስተው ለትግራይ ትይዩ ከሚሆን ሐማሴን ከሚባለው ሀገር ሲደርሱ በምሥራቅ በኩል ከፍተኛ ተራራ ተመለከቱና ወደ ተራራው ሄዱ። ጌታም በተራራው ላይ ሳሉ እናቱን እንዲህ አላት ይቺ ተራራ ምስጋናሽ የሚነገርባት ቦታ ትሆናለች። የተራራዋም ስም ደብረ ሃሌ ሉያ ወይም ደብረ ዳሞ ይባላል። ትርጓሜውም የአምላክ ልጅ የመስቀሉ ቦታና የስሙ መገኛ ወይም አደባባይ ማለት ነው።ከዚያም በኋላ ታቦተ ጽዮን ወደምትኖርበት ወደ አክሱም ደረሱ። ታቦተ ጽዮን ባለችበት ቦታ ሳሉ ባዚን የተባለው የኢትዮጵያ ንጉሥ ታቦተ ጽዮንን ለመሳለም መጣ። የካህናቱ አለቃ አኪን ለንጉሡ የኢሳይያስን መጽሐፍ አነበበለት። የተነበበውም የመጽሐፍ ክፍል ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ወንድ ልጅ ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች የሚል ነበር። ስደተኞቹ ግን ለንጉሡም ሆነ ለካህናቱ ሳይገለጡ የመጽሐፉን ቃል ከሰሙ በኋላ በደመና ተጭነው ወደ ደብረ ዐባይ ሄዱ ። ጌታም እናቱን እንዲህ አላት ይህች ሀገር እንደአክሱም ለስምሽ መጠሪያ ርስት ትሁን በኋላ ዘመን በቀናች ሃይማኖት ጸንተው ሕጌን የሚያስተምሩ አንቺን የሚወዱ ሰዎች ይኖሩባታል። ከዚያም በኋላ ከደብረ ዐባይ ተነስተው ዋሊ ወደ ሚባለው ገዳም /ወደ ዋልድባ / ሄዱ። በዋልድባ በረሃም ሳሉ በራባቸው ጊዜ ጌታ በዮሴፍ ብትር የአንዱን ዕንጨት ስር ቆፈረ። ሦስት መቶ አስራ ስምንት ስሮችን አወጣና ለእናቱ ብይ ብሎ ሰጣት። እናቱም ይህን የሚመር ዕንጨት አልበላም አለችው። ጌታም በኋላ ዘመን ስምሺን የሚጠሩ አንቺን የሚያከብሩ ብዙ መናንያን ይህን እየበሉ በዚህ ቦታ ይኖራሉ። ዕንጨቱም የሚጣፍጥ ይሆንላቸዋል አላት። ከዚህ በኋላ በደመና ተጭነው ከዋልድባ ወደ ጣና የባሕር ወደብ ሄዱ። በጣና ደሴትም ደጋግ ሰዎች ተቀብለዋቸው ሦስት ወር ከአስር ቀን ተቀመጡ። የኢትዮጵያ ሰዎች በደስታ ተቀብለዋቸዋል እንደ ግብፃውያን አላሰቃዩአቸውም ። በጥር አስራ ስምንት /፲፰/18/ ቀን ዑራኤል መጥቶ የሄሮድስን መሞት ነገራቸው ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ዘንድ በደመና ከተጫኑ በኋላ ጌታ እናቱን እንዲህ አላት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ተራራዎች ሁሉ ለስምሽ መታሰቢያ ይሆኑሽ ዘንድ አሥራት አድርጌ ሰጥቼሻለሁ ። ብሎ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ተራራዎችን ሜዳዎችን ኮረብታዎችን አሳያት። እመቤታችን ሁሉንም ቦታዎች እየተዘዋወረች እንድታይ ልጅዋን ጠየቀችው። ልጅዋም የሚመለሱበት ጊዜ እንደደረሰ ነገራት። በብሩህ ደመና ላይ ተቀምጠው ክፍላተ አህጉር እየተዘዋወሩ ተራራዎችን ወንዞቸን አስጐበኛት የኢትዮጵያን ምድር ከጐበኙ በኋላ በደመና ተጭነው ጥር ፳፱/29 ቀን ምድረ ግብፅ ደረሱ። ወደ ኢትዮጵያ የገቡት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው። ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ የመግባት ታሪክ በድርሳነ ዑራኤል ላይ በስፋት ተጽፏል።
❖ የሊቀ መለአክት ቅዱስ ዑራኤል ፀሎት በያለንበት ይድረስ! በረከት ረድኤቱ ይደርብን!ምልጃ ጥበቃዉ አይለየን!❖