https://www.bitchute.com/video/KQmzqw0UpmB5/
😇 እንኩዋን ለታላቁ ሊቅ "ቅዱስ ያሬድ" ዓመታዊ በዓል አደረሰን ✞✞✞
የዛሬው ግንቦት ፲፩/11 ዕለት ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበት አመታዊ ክብረበዓል ነው።
😇 Today, Ginbot ፲፩/11, ፳፻፲፰/2018 (May 19, 2026) marks the departure of St. Yared, the great Ethiopian composer, Saint Yared, who disappeared at the age of 66.
😇 Saint Yared, the legendary 6th-century Axumite composer credited with creating the liturgical music and chant tradition (Zema) of the Ethiopian and Eritrean Orthodox Churches, is believed by tradition to have disappeared rather than died.
His disappearance is surrounded by rich spiritual tradition:
• The Departure: On May 19, 571 AD (Ginbot 11 on the Ethiopian calendar), after serving the church and praising God, Yared sought to withdraw from the world. According to hagiography, he stood before the Tabernacle of Zion in Axum and prayed, after which he was raised above the ground and transported away.
• The Location: He is said to have departed to the desert and the mountains, specifically living a life of fasting and prayer in the wilderness. Some traditions state he spent his final days in the Debre Hawi monastery in the northern mountains.
• Legacy: The exact location of his grave remains unknown to this day. His monumental contributions—including the development of the Digua (hymn books) and a unique musical notation system—are commemorated annually by the church on his feast day.
🎶 Long Before This Form of Musical Notation Began in The West, There Was a Composer in Ethiopia
https://www.bitchute.com/video/CA961Pd6HnnR/
😇 The First Great Master of The Style Was The Composer Saint Yared
https://www.bitchute.com/video/Okr1PZVGZayJ/
🐦 Three Little Birds: Saint Yared’s Inspiration From Above
😮 ልዩና ብሩክ በሆነው በዛሬው ዕለት አንድ ያስገረመኝ፣ ያስደሰተኝና ለሤረኞቹ ያሳዘነኝ ክስተት፤ በ'አዲስ ኢትዮጵያ' ዩቲውብ ቻነሌ ከአራት ዓመታት በፊት በፍልሰታ ዕለት ልኬው የነበረውን ቪዲዮ ሤረኞቹ የፋሺስቱ ጋላ-ኦሮሞ እስላማዊ አገዛዝ ባሪያዎች ማስነሳታቸውና 'ኮፒ ራይት ስትራይክ' ማሰጠታቸው ነው። ሆን ተብሎ ልክ በቅዱስ ያሬድ ዕለት። ስለ ሤረኛው ጋላ-ኦሮሞ አጋራቸው ስለ 'እፎይ' ማስጠንቀቅ በመጀመሬ... በቪዲዮው የዘማሪ 'ቀሲስ' እንግዳወርቅ በቀለ 'ደጅ ጠናሁ ሜዲያ'(ኦሮማራ ወይም ጋላ-ኦሮሞ ነውን?) አንድ መዝሙር ስለገባበት ፈልፍለው በማውጣት ስትራይክ አስጡት! አይይይ! በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ላይ ጀነሳይዳዊ ጂሃድ በመክፈት ከሚሊየን በላይ የቅዱስ ያሬድን ልጆችን መጨፍጨፉ አልበቃቸውም ያው በማህበራዊ ሜዲያም ቤተሰቦቹን በዚህ መልክ ማሳደዱን ቀጥለውበታል። ከሰባት ዓመታት በፊት ብዙ ተከታዮች የነበሩትን የቀደመውን የ'አዲስ ኢትዮጵያ' ቻኔል ልክ በፋሲካ ትንሣኤ ዕለት ያስነሱትም እነ 'ቋንቋየነሽ፣ ዘመድኩን በቀለ፣ 'አቡነ' ፋኑኤል' ነበሩ። ለእኔ ትልቅ ምልክት ነው፤ ደስ ብሎኛል...ለእነርሱ ግን ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!
የጻድቁ አባታችን የቅዱስ ያሬድ ረድኤትና በረከት ከሀገራችን ከኢትዮጵያና ከህዝቧም ጋር ይሁን አሜን።
አበው ቅዱስ ጳውሎስ በሁለተኛ ቆሮንቶስ መልዕክቱ ላይ "እንዲህ ያለው ሰው ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ ። እንዲህ ያለውንም ሰው አውቃለሁ ። በሥጋ እንደ ሆነ ወይም ያለ ሥጋ እንደሆነ አላውቅም ። እግዚአብሔር ያውቃል ። ወደ ገነት ተነጠቀ ። ሰውም ሊናገር የማይገባውን ፤ የማይነገረውን ቃል ሰማ ።"2ቆሮ. 12፥2-5 ብሎ የተናገረው ለቅዱስ ያሬድ ነው ብለውም ይተረጉሙታል ።
ግዕዝ ፣ እዝል ፣ ዓራራይ ተብለው የተወሰኑ ሰማያዊ የዜማ ስልቶችንም የተማረው ከእግዚአብሔር ነው ። ሊቁ ማኅሌታይ ወደ ምድር ተመልሶ በታላቅ ተመስጦ አክሱም ጽዮን ማርያም ውስጥ በሃሌታ አመሰገነ ። ሕዝቡና ንጉሡም አፄ ገብረ መስቀል ከዜማው ጣዕም የተነሳ አደነቁ ። ቅዱስ ያሬድ ዜማውን በንጉሡ ፊት ሲያቀርብ ንጉሡ በተመስጦ እግሩን በጦር ቢወጉትም የዜማው አቅራቢው ቅዱስ ያሬድም ሆነ ዜማውን የሚሠሙት ንጉሥ ገብረ መስቀል ዝማሬው እስኪያልቅ ድረስ የተፈጠረውን አደጋ አላዩትም ነበር ። ሁሉም በተመስጦ ላይ ነበሩና ።
የቅዱስ ያሬድ ዜማዎች በህግ የሚዜሙ ባለምልክቶች ናቸው። ምልክቶቹ «ኖታ» ከሚባለው የአውሮፓውያን የዜማ ስልት ጋር ይወዳደራሉ ። ከላይ እንደተገለጸው ሊቁ የደረሳቸው የዜማ አይነቶች ግዕዝ፤ እዝል እና አራራይ በመባል ይታወቃሉ። ሶስቱም ዜማዎች መሀትው ዋዜማ፤ ስልጣን፤ እስመለአለም፤ አቡን ቅንዋትና ሰላም የሚባሉ መጠሪያ ስሞችም አሏቸው። ዜማዎቹ ልዩ ልዩ ስልቶችን የያዙ ሲሆን አጫብር፤ ቆሜ፤ አሮጌ ቤተልሄም፤ አዲስ ቤተልሄምና ተጉለቱ በመባል ይታወቃሉ።
የዜማዎቹ ስልቶች በተለያዩ ድምፆች፣ በጭንቅላት፣ በአፍንጫና በጉሮሮ ይዜማሉ። በዚህ ሂደትም አራተኛ አቋቋም የሚባለው ስልት ጥሩ የዜማ መገለጫ ስለመሆኑ በዘርፉ በጥናት ውስጥ ያለፉ ሊቃውን አባቶች ይመሰክራሉ። ይህ ዜማ ታች ቤት፣ ላይ ቤት፣ ሳንኳና ተክሌ ሰቆጤ በሚሉ መጠሪያዎች በተለይ በጎንደር አካባቢ ጥቅም ላይ እንደሚውል ይነገራል።
በቅዱስ ያሬድ የዜማ ስልት የሚቃኙት ካህናትም በዝማሜ በመረገድ፤ በፅናፅልና በከበሮ ያሸበሽባሉ። የዘንጋቸው አወዛወዝና አጣጣል የፅናፅሉ አወራረድና አመላለስ እንዲሁም የከበሮ አመታቱ በሦስት የተከፈለ ሲሆን መደበኛ ስሞቹም ንዑስና ዓብይ፣ መረግድ፣ ድፋት ለዘብና ማህሌተ ገንቦ ይባላሉ። አእምሮን ከሚያነቃቁና መንፈስን ከሚማርኩ ዜማዎች መካከልም በተለይ ለዘብና ማህሌተ ገንቦ የተሰኙት ዝማሬዎች እጅግ ጥዑም የሆኑና ለሚሰማውም ደስ የሚያሰኙ የዜማ ስልቶች ናቸው።
ድጓ ፣ ጾመድጓ ፣ ምዕራፍ ፣ ዝማሬና መዋሰዕት የተባሉ አምስት መጻሕፍትን ደርሶ ለቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያበረከተው ቅዱስ ያሬድ ታላቅ ደራሲም ነው ። ሊቁ ማኅሌታይ፤ ጥዑመ ልሳን ፣ ንሕብ ፣ ሊቀ ሊቃውንት ፣ የሱራፌል አምሳያ ፣ የቤተ ክርስቲያን እንዚራ ፣ ካህነ ስብሐት፣ መዘምር ዘበድርሳን ፣ ማኅሌታይ ፣ ልዑለ ስብከት እያሉ የሚጠሩት ሊቁ ማኅሌታይ በአክሱም ጽዮን እና በደብረ ዳሞ አገልግሏል ። በጣና ቂርቆስ እና በዙር አባ አቡነ አረጋዊ ገዳምና በሌሎች የኢትዮጵያ ገዳማትም ወንበር ዘርግቶ ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርቷል ።
ቅዱስ ያሬድ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዜመው «ሀሌ ሉያ ለአብ፣ ሀሌ ሉያ ለወልድ፣ ሀሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ፣ በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድር፣ ወበዳግም አርእዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ሲል ነበር። ይህን ዜማ ሲቀኝም ህዝቡ እሱን ለማዳመጥ ሀገር አቋርጦ ይመጣ እንደነበር መዛግብት ያስረዳሉ። ይህ ሁኔታም ያልተለመደ በመሆኑ እንደትንግርት ይቆጠር ነበር። የዜማው አወራረድ ተሰምቶ አይጠገብም። በዘመኑ የነበሩት ንጉሥ አፄ ገብረ መስቀል በቅዱስ ያሬድ መንፈሳዊ ዜማ በመደነቃቸው ዜማው በአዋጅ ጸድቆ ሥራ ላይ እንዲውል መፍቀዳቸው ይነገራል።
ያሬድ የንጉሡ የቅርብ ሰውና ወዳጃቸውም ነበር። እሳቸውም ሹመት ሊሰጡት ደጋግመው ጠይቀውታል። ይሁን እንጂ መንፈሱ በምናኔና ዓለምን በመናቅ የተሞላ ስለነበር ጥያቄያቸውን ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም። አንድ ቀን ግን ጻድቁ ቅዱስ ያሬድ ንጉሡን «በምናኔ በሰሜን ገዳም እንድኖር ይፍቀዱልኝ» ሲል ጠየቃቸው። እርሳቸውም ሀሳቡን ተቀብለው ፈቀዱለት። ቅዱስ ያሬድ በአክሱምና በደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ ገዳም ለረጅም ጊዜያት በትጋት ደቀ መዛሙርትንም በማፍራት አገልግሏል ።
ጻድቁም ወደ ሰሜን ተራሮች ወደ ራስ ደጀን ከመሄዱ በፊትም ታቦተ ጽዮንን ለመሰናበት ከመቅደስ ገባና ከመሬት ክንድ ከስንዝር ከፍ ብሎ በመቆም ዛሬ ሁላችን በውዳሴ ማርያም የጸሎት መጽሐፍ መጨረሻ ላይ የምንጸልየውን "አንቀፀ ብርሃን" የሚባለውን የምስጋና ጸሎት ንባቡን ከነ ዜማው ደርሶ ለቤተ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አበረከቶልን ከንጉሥ አፄ ገብረመስቀል ፈቃድ ያገኘው ጻድቁ ቅዱስ ያሬድም የመጨረሻዎቹን የዚህ ምድር ላይ ቆይታውን በሰሜን ተራሮች አካባቢ በበረዶማው የራስ ደጀን ተራራ ላይ ለማድረግ ሄዷል ። በዚያም በዋሻ ተቀምጦ በትጋሃ መላእክትና በተባሕትዎ በድንግልና ሲያገለግል ፤ ተተኪ ደቀመዛሙርትንም ሲያፈራ ቆይቶ በመጨረሻም ግንቦት 1 ቀን በ576 ዓም በተወለደ በ71 ዓመቱ ተሰውሯል።
አሳዛኙ ነገር እንዲህ ያለው ሊቅ ፣ ጻድቅና ቅዱስ የዜማና የመጻሕፍት ደራሲ የሆነው አባት ቅዱስ ያሬድ በሀገሩ በኢትዮጵያ የቀድሞው መንግሥት በስሙ ከሰየመለት የሙዚቃ ትምሕርት ቤት በቀር በክብሩ መጠን የተደረገለት አንድም ማስታወሻ የሚሆን ነገር በሀገሩ ላይ የለም ። ይህ የሆነው ደግሞ የቅዱስ ያሬድም ሆነ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ትልቁ በደላቸው ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ብቻ ነው ።
አቤት አቤት ቅዱስ ያሬድ አውሮፓዊ ቢሆን ኖሮ ብዬ ሳስብ ምን ሊያደርጉት እንደሚችሉ መገመት ብቻ ነው ። መንገዱ ፣ አደባባዩ ፣ ተራራው ፣ ትምህርት ቤቱ ፣ ቁሳቁሱ ሳይቀር በስሙ በተሰየመ ነበር ። አንድ ፒያኖ ይዘው ኦርኬስትራ ለመሩ ሰዎች ተአምር ለመፍጠርና ስማቸውን በመሸጥ የሀገር ገቢ ማግኛ ሲያደርጉ ሳይ እደነቃለሁ ። በጀርመን ሀገር በቦን ከተማ የቤትሆቨን ቤትን ለመጎብኘት ሄጄ ቅዱስ ያሬድን ሳስበው አልቅስ አልቅስ ነበር ያለኝ ። ሰው ቢልዮን ዶላር የሚያስገባለትን ሀብት ከመጋረጃ ጀርባ ደብቆ እንዴት በድህነት ይማቅቃል?? በቅዱስ ያሬድ አፍሮ በማያውቀው ፑሽኪን ይመጻደቃል ።
ኢትዮጵያ ለማታውቀው ፑሽኪን ለተባለ ሩሲያዊና ደጎል ለተባለ እንግሊዛዊው ግለሰቦች አደባባይ ስትሰይም ፣ ለአቶ ቸርችል ጎዳና ፣ ለጀናራል ዊንጌት ደግሞ ትምሕርት ቤት በመሥራትና በመሰየም ያልበላትን ስታክ ትታያለች ። በአቡነ አረጋዊ ስም ቡና ቤት ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ቢራ ለመሰየም ግን ቅሽሽ አይላትም ፤ የሚጠየፍና ሃይ ባይም ትውልድ የለም ።
አንድ የውጭ ሀገር ሰው ኢትዮጵያ ሄጄ ስለ ቅዱስ ያሬድ ላጥና ቢል መከራውን ነው የሚበላው ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በሕይወት ለመኖሯ እና በምድር ላይ እንድትቀጥል ካደረጓት ነገሮች አንዱና ዋነኛው የቅዱስ ያሬድ ሥራዎች መኖር ነው ። ያለ ቅዱስ ያሬድ ሥራዎች ቤተክርስቲያናችን ማሰብ በራሱ ከባድ ነው የሚሆነው ። ቅዱስ ያሬድ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ፣ ለሊቃነ ጳጳሳቱ ፣ ለካህናትና ለዲያቆናቱ ፣ ለመዘምራኑም ሁሉ ፤ ሞገስ ፣ ክብር ፣ እንጀራም ጭምር ነው ። ነገር ግን ይኽን ሁሉ ለሆነላቸው ጻድቅ አንዳቸውም አስታውሰው ግዙፍ ነገር በስሙ ሊሠሩ ሲነሳሱ አይታዩም።
🎶 እነ ሞዛርት ከመወለዳቸው ሺህ ዓመታት አስቀድሞ፡ ሊቁ ማኅሌታይ አባታችን ቅዱስ ያሬድ በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያችን ተወለደ
😇 ስለ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አብዛኛው ይህ ሥጋዊ ዓለም ምንም እውቀት የለውም/ማወቅም አይፈልግም። ምክኒያቱም፤ ቅዱስ ያሬድ በመንፈሳዊው ዓለም ብቻ ሊሰማ የሚችል እጅግ በጣም የተራቀቀ የዜማ ጥበብ አባት በመሆኑ ነው። ሥጋውያኑ ኤዶማውያኑ አፍሪካዊው/ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ የእነ ሞዛርትን እና ቤትሆቨንን ቦታ የሚነጥቅባቸው ከእነርሱ የላቀ የዜና ደራሲ፣ አቀናባሪ እና ምሁር ሆኖ ስላገኙት ነው። የመንፈሳዊ ማንነትና ምንነት ቢኖራቸው ኖሮማ በየሙዚቃ ትምህርት ቤቱ ስለ ቅዱስ ያሬድ ውብ ዜማዎችን እና ማስታዎሻዎቻቸውን ባስተማሩ ነበር። በተገላቢጦሽ ግን የእኛ ትምህርት ቤቶች የአውሮፓውያኑን ያስተምራሉ።
ቅዱስ ያሬድ:- ከእግዚአብሔር ያገኘነው አባታችን፤
ክብራችን: ሞገሳችን ነውና በምን እንመስለዋለን? አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም): ልቡናው የቅድስና ማሕደር: ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ ነው። እስከ አርያም ተነጥቆ የማይፈጸም ምሥጢርን የተመገበ ማን እንደርሱ!
ቅዱስ ያሬድ ለኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ: ሙሉ አካሏ ነው። ታዲያ በተለይ በእነዚህ በያዝናቸው አራት ዓመታት ከባዕዳውያኑ ኤዶማውያኑ እስማኤላውያን እና ከዋቄዮ-በዓል-አላህ-ባፎሜት-ሉሲፈር ባሪያዎች ጋር አብራችሁ በ ቅዱስ ያሬድ ትውልድ ከተማ በቅድስት አክሱም ጽዮን ላይ የዘመታችሁ ሁሉ ዛሬም የመመለስ ጭላንጭል እንኳን እያሳያችሁ አይደለም፤ የንሰሐው ጊዜም እያለቀባችሁ ነው፤ እንግዲህ ወዮላችሁ! ወዮላችሁ! ወዮላችሁ!
አውሮጳውያኑ የዜማ ሊቃውንት ሞዛርትና ቤትሆቨን ከመወለዳቸው ሺህ ዓመታት አስቀድሞ በኢትዮጵያችን የተወለደ ነው ሊቁ ማኅሌታይ አባታችን ቅዱስ ያሬድ። ጻድቁ የተወለደው በ ፭፻፭/ 505 ዓ/ም አክሱም ጽዮን አቅራቢያ ሲሆን አባቱ ይስሐቅ (አብድዩ ) እናቱም ክርስቲና (ታኡክልያ) ይባላሉ።
ይህን ዘመን በጥሞና ልናጠናው ይገባናል። በእኔ በኩል እንደሚታየኝ፤ አክሱማዊቷ ኢትዮጵያ በዚህ ዘመን (ንጉሠ ነገሥታት አብርሐ እና አጽበሐ፣ ንጉሥ ካሌብ...) ነበር በሁሉም መስከ ከፍታዋ መታየት ጀምሮ የነብረው። በሃይማኖት እና መንፈሳዊ ሕይወት፣ በሥነ ጥበብ፣ ሥነ ጽሑፍ እና ዜማ ፥ በምጣኔ ኃብት፣ እርሻ እና ንግድ፣ በሕንፃ፣ ዋሻ እና መርከብ ግንባታዎች ሮማውያኑን እና አጋሮቻቸውን ያስደነቁ፣ ያስቀኑ እና ያስፈሩ ነበሩ። ስለዚህ የምስራቅ ሮማ (ቁስጥንጥንያ) ነገሥታት አክሱማዊቷን ኢትዮጵያ ለማዳከም ያልጠነሰሱት ሤራ አልነበረም። ይህም ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ በኋላ ላይ ከፍተኛ ውድቀትን፣ መራቆትን፣ ድኽነትን፣ ክፉኛ ወረርሽኞችን ሁሉ አምጥቶባቸዋል።
😇 ኢትዮጵያን ከፍ የሚያደርጓት እነ ቅዱስ ያሬድ እየመጡ ነውና ተዋሕዷውያን ወደ አንድ እንሰባሰብ
💭 ሁሉም ከጸዳ በኋላ ቅዱስ ያሬድ በስውር እያሰለጠናቸው ያሉት ትክክለኛዎቹ ካህናት ይወጣሉ፤
እውነተኞቹን ተዋሕዶ ክርስቲያኖችን የሚሰበስብ፣ ክርስቶስን የሚወድና እስልምናን የሚጠላ አንድ ቅዱስ ሰው በእግዚአብሔር ተቀብቶ ይወጣል። ያኔ የእስልምና አምልኮ ከምድረ ገጽ ይጠፋል። እውነተኞቹ ኢትዮጵያን የሚያውቋት ያውቁታልና ወደ አንድ ይሰባሰባሉ። መቶ ሚሊየን የሚሆነው ነዋሪ ኢትዮጵያን አያውቃትምና ሁሉም ይጠፋል። በአፋቸው ሳይሆን በህሊናቸው ኢትዮጵያንና ተዋሕዶን ከልባቸው የያዙት፣ ደሞዝ እየተከፈላቸው ካህናት የሆኑት ሳይሆኑ፣ በደሞዙ የሚንጠራሩት ሳይሆኑ፣ በዘረኝነት የተለከፉት ሳይሆኑ፣ ዘረኛ፣ ዘማዊና ጉቦኛ ያልሆኑት፣ ዘረኛ ያልሆኑትንና በፍቅር የሚመላለሱትን ምዕመናንን ጨምሮ ሁሉም በቅዱሱ ሰው ዙሪያ ተሰባስበሰው ኢትዮጵያን ይኖሩባታል።
†††[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፲፩፥፮]†††
“ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይቀመጣል፥ ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል፤ ጥጃና የአንበሳ ደቦል ፍሪዳም በአንድነት ያርፋሉ፤ ታናሽም ልጅ ይመራቸዋል።”
❖❖❖ይህ ዓለም ካዘጋጀልን ወጥመድና መከራ ሰውሮ ወደ አንድነት ይሰብስበን!❖❖❖
†††[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፲፩]†††
፩ ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል።
፪ የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
፫ እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል። ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም፤
፬ ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፥ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል፤ በአፉም በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
፭ የወገቡ መታጠቂያ ጽድቅ፥ የጎኑም መቀነት ታማኝነት ይሆናል።
፮ ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይቀመጣል፥ ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል፤ ጥጃና የአንበሳ ደቦል ፍሪዳም በአንድነት ያርፋሉ፤ ታናሽም ልጅ ይመራቸዋል።
፯ ላምና ድብ አብረው ይሰማራሉ፥ ግልገሎቻቸውም በአንድነት ያርፋሉ፤ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል።
፰ የሚጠባውም ሕፃን በእባብ ጕድጓድ ላይ ይጫወታል፥ ጡት የጣለውም ሕፃን በእፉኝት ቤት ላይ እጁን ይጭናል።
፱ በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ አይጐዱም አያጠፉምም፤ ውኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።
፲ በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ለአሕዛብ ምልክት ሊሆን የቆመውን የእሴይን ሥር አሕዛብ ይፈልጉታል፤ ማረፊያውም የተከበረ ይሆናል።
፲፩ በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ የቀረውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦርና ከግብጽ፥ ከጳትሮስና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላምና ከሰናዖር ከሐማትም፥ ከባሕርም ደሴቶች ይመልስ ዘንድ ጌታ እንደ ገና እጁን ይገልጣል።
፲፪ ለአሕዛብም ምልክትን ያቆማል፥ ከእስራኤልም የተጣሉትን ይሰበስባል፥ ከይሑዳም የተበተኑትን ከአራቱ የምድር ማዕዘኖች ያከማቻል።
፲፫ የኤፍሬምም ምቀኝነት ይርቃል፥ ይሑዳንም የሚያስጨንቁ ይጠፋሉ፤ ኤፍሬምም በይሑዳ አይቀናም፥ ይሑዳም ኤፍሬምን አያስጨንቅም።
፲፬ በምዕራብም በኩል በፍልስጥኤማውያን ጫንቃ ላይ እየበረሩ ይወርዳሉ፥ የምሥራቅንም ልጆች በአንድነት ይበዘብዛሉ፤ በኤዶምያስና በሞዓብም ላይ እጃቸውን ይዘረጋሉ፥ የአሞንም ልጆች ለእነርሱ ይታዘዛሉ።
፲፭ እግዚአብሔርም የግብጽን ባሕር ያጠፋል፤ በትኩሱም ነፋስ እጁን በወንዙ ላይ ያነሣል፥ ሰባት ፈሳሾችንም አድርጎ ይመታዋል፥ ሰዎችም በጫማቸው እንዲሻገሩ ያደርጋቸዋል።
፲፮ ከግብጽም በወጣ ጊዜ ለእስራኤል እንደ ነበረ፥ ለቀረው ለሕዝቡ ቅሬታ ከአሦር ጐዳና ይሆናል።
No comments:
Post a Comment