Friday, November 27, 2026

Apostle Philip & Ethiopian Eunuch | Christianity First Entered Ethiopia in 34 AD via The Road Between Jerusalem & Gaza

https://www.bitchute.com/video/txm6CAOz8bJ0/

https://rumble.com/v7j08m4-apostle-philip-and-ethiopian-eunuch-christianity-entered-ethiopia-in-34-ad-.html

😇 ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስና ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ስምዖን ባኮስ | ክርስትና ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የገባው በ፴፬/34 ዓ.ም. በኢየሩሳሌምና በጋዛ መካከል ባለው መንገድ በኩል ነው።

ወንጌላዊው ፊልጶስ በመጽሐፍ ቅዱስ (የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፰)መሠረት ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ በማስተማርና በማጥመቅ የክርስትና ብርሃን ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ ትልቅ ሚና የተጫወተ ቅዱስ ነው።

😇
የሐዋርያው ፊልጶስና የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ግንኙነት

•
የመንፈስ ቅዱስ መሪነት፡ ፊልጶስ በሰማርያ ወንጌልን ከሰበከ በኋላ፣ የጌታ መልአክ በመንገድ ላይ እንዲሄድ መራው።
•
ትምህርትና ጥምቀት፡ በመንገዱ ላይ የኢትዮጵያ ንግሥት (ሕንደኬ) ገንዘብ ጠባቂ የነበረውን ጃንደረባ ስምዖን ባኮስን አገኘ። ጃንደረባው የነቢዩ ኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ አግኝቶ፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚገልጸውን ምሥራች አብራራለትና በውኃ አጠመቀው።
•
የወንጌል መስፋፋት፡ ከጥምቀት በኋላ ጃንደረባው ስምዖን ባኮስ ደስ ብሎት ወደ ሀገሩ መመለሱ ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ለመግባቱ መሠረት እንደሆነ ይታመናል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትውፊት

•
መታሰቢያና ክብር፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ፊልጶስ የክርስትናና የጥምቀት መሠረት ከሆኑ ቅዱሳን አንዱ ተደርጎ ይከበራል። የዕረፍት በዓሉ ጥቅምት ፲፬/14 ይከበራል።
•
አብያተ ክርስቲያናት፡ በስሙ የተሰየሙ አብያተ ክርስቲያናትና ካቴድራሎች (ለምሳሌ ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊልጶስ ካቴድራል) በሀገሪቱ ይገኛሉ።

😇 ቅዱስ ሐዋርያ ፊልጶስ

ኅዳር ዐሥራ ስምንት/፲፰፤ በዚችም ዕለት ከአባቶቻችን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ ሐዋርያ ፊልጶስ በሰማዕትነት የሞተበት መታሰቢያው ነው።

ይህም እንዲህ ነው ዕጣው ወደ አፍራቅያና ወደ አውራጃዋ ሁሉ በወጣ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በውስጧ ሰበከ።

ልቡናንም የሚያስደነግጥ ድንቆች ታምራቶችንም አደረገ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ እግዚአብሔርንም ወደ ማወቅ ከመለሳቸው በኋላ ወደሌሎች ብዙ አገሮች ወጣ እያስተማረ ሰዎችን ወደ ሃይማኖት ሲጠራ ኖረ።

ከዚህም በኋላ ወደ ሌላ አገር ሒዶ የከበረ ወንጌልን ሰበከላቸው ብዙዎቹም ክብር ይግባውና በጌታችን አመኑ ያላመኑት ግን ይገድሉት ዘንድ ተማከሩ በንጉሥም ዘንድ ተወዳጅነትን ያገኙ ዘንድ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ሐዋርያ ፊልጶስን ይዘው አሠሩት ጽኑዕ ሥቃይንም አሠቃዩት እርሱም ይስቅባቸውና ከዘላለም ሕይወት ለምን ትርቃላችሁ የነፍሳችሁንስ ድኅነት ለምን አታስቡም ይላቸው ነበር እነርሱ ግን ብዙ ካሠቃዩት በኋላ ዘቅዝቀው ሰቀሉት ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ።

ሥጋውንም በእሳት ሊአቃጥሉ በወደዱ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ከእጆቻቸው መካከል ነጠቃቸው እነርሱም ወደርሱ እየተመለከቱ ወስዶ ከኢየሩሳሌም አገር ውጭ አግብቶ ሠወረው ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው ሁሉም በታላቅ ድምፅ የቅዱስ ፊልጶስ አምላክ አንድ ነው እያሉ ጮኹ አሠቃይተው ስለገደሉትም ተጸጽተው አዘኑ ክብር ይግባውና በጌታችንም አመኑ።

የቅዱስ ሐዋርያ ፊልጶስንም ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ለመኑት ሰውን የሚወድ ቸር ይቅር ባይ ጌታችንም ልመናቸውን ተቀብሎ የሐዋርያ ፊልጶስን ሥጋ መለሰላቸውና እጅግ ደስ አላቸው ሁሉም ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት ገቡ ከሐዋርያውም ሥጋ ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታችን ሐዋርያ ፊልጶስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

♰ In the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, November 27, 2026 corresponds to 18 Hedar (Hidar 18) on the Ethiopian calendar, which commemorates (martyrdom) Saint Philip the Apostle (one of the Twelve Apostles).

• Apostolic Tradition: Ethiopian Orthodox tradition traces the beginning of Christianity in Ethiopia to the 1st century around (34 AD) , when Philip the Evangelist baptized an Ethiopian official, Simeon Bachos on the road between Jerusalem and Gaza (Acts 8:26–39)

• 4th-Century Establishment: While the New Testament does not state that the official founded a church organization, Christianity took broad institutional hold in the 4th century AD when King Ezana adopted it as the official religion of the Axumite Empire.

Philip the Evangelist, mentioned in the Book of Acts, played a vital role in spreading the gospel during the early days of the church. Known for his bold preaching, miracles, and encounter with the Ethiopian eunuch, Philip exemplified obedience to the Holy Spirit and dedication to Christ’s mission.

In this video, we delve into Philip’s ministry, his role in the spread of Christianity beyond Jerusalem, and the significance of his work as one of the seven deacons chosen to serve. Discover how Philip’s story inspires us to share the good news with others and follow the Spirit’s guidance.

😇 Ebed Melech the Ethiopian: The Unsung Hero Who Defied All to Save God’s Prophet

https://www.bitchute.com/video/tFtdDTXFfxgs/

https://rumble.com/v6g72pp-ebed-melech-the-ethiopian-the-unsung-hero-who-defied-all-to-save-gods-proph.html

😇 ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ፤ የእግዚአብሔርን ነብይ ለማዳን ሁሉንም የተገዳደረው ያልተነገረለት ጀግና

Uploading: 97694 of 97694 bytes uploaded.

No comments:

Post a Comment

Apostle Philip & Ethiopian Eunuch | Christianity First Entered Ethiopia in 34 AD via The Road Between Jerusalem & Gaza

https://www.bitchute.com/video/txm6CAOz8bJ0/ https://rumble.com/v7j08m4-apostle-philip-and-ethiopian-eunuch-christianity-entered-ethiopia-i...