❖❖❖ ጸሎተ ሐሙስ በቅድስት ልደታ ማርያም + መድኃኔ ዓለም ዓብያተ ክርስቲያናት ፤ አክሱም ጽዮናውያን ከመባረራቸውና የእግዚአብሔር መንፈስ ከመራቁ በፊት❖❖❖
😇 ጌታችን በጸሎተ ሐሙስ | ሌባን እንደምትይዙ በሰይፍና በጎመድ ልትይዙኝ መጣችሁን?
ከኅፅበተ እግር በኋላ ሊይዙት ወደ እርሱ የመጡትን የካህናት አለቆችን፣ የቤተ መቅደስ ሹሞችንና ሽማግሌዎችን ጌታችን እንዲህ ብሏቸዋል፤ "ሌባን እንደምትይዙ በሰይፍና በጎመድ ልትይዙኝ መጣችሁን? ዘወትር ከእናንተ ጋር በቤተ መቅደስ ስኖር እጃችሁን እንኳ አልዘረጋችሁብኝም፤ ነገር ግን ጊዜያችሁ ይህ ነው፡፡ የጨለማው አበጋዝም ሥልጣኑ ይህ ነው፤" (ሉቃ. ፳፪፥፶፪-፶፫)።
👉 የሰሙነ ሕማማት ሐሙስ ፮ ስያሜዎች
፩. ሕጽበተ እግር ይባላል
፪. የጸሎት ሐሙስ ይባላል
፫. የምስጢር ቀንም ይባላል
፬. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል
፭. የነጻነት ሐሙስ ይባላል
፮. አረንጓዴው ሐሙስ ይባላል
No comments:
Post a Comment