https://www.bitchute.com/video/T2WIbY4TS2zC/
♰ ድንቁ ርዕሠ አድባራት እንጦጦ ደ/ኃ/ቅ ራጉኤል ወ ኤልያስ ቤ/ክርስቲያን
😇 እንኳን ለ ለታላቁ ነብይ ለቅዱስ ኤልያስ ዓመታዊ ክብረ በዓል (የልደት ቀን)፣ ለወርሃዊ የቅድስት ልደታ ማርያም እና የሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል መታሰቢያ ዕለት አድረሰን! አደረሳችሁ!
👉 ቀደም ሲል ባቀረብኩት ቪዲዮ የሚከተለውን ጽሑፍ አጋርቼ ነበር፤
“ባለፉት ስድስት ወራት ከነብዩ ኤልያስ፣ ነብዩ ሔኖክ፣ ከፓትርያርክ አባታችን ቅዱስ ሔኖክ፣ ከቅዱስ ራጉኤልና ቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በተያያዘ ተዓምር ልላቸው የምችላቸውን አስገራሚ ክስተቶች እየታዘብኩ ነው። በዚህች ምድራችን ላይ ብቻ ሳይሆን በተለይ ፀሐይ ላይ የሆነ ዓለምን ሊለውጥ የሚችል ክስተት በእነዚህ ቀናት እየታዘብን ነው። ከእነ ነብያቱ ሔኖክ እና ኤልያስ መምጣት ጋር የሚገናኝ ክስተት ይሆን? የሆነ ትልቅ ነገር ይሰማኛል!”
🌞 ሰሞኑን ስለ ፀሐይ ፍንዳታ ብዙ እየተወራ እና እየተፈራ ነው (የሆነ የሙቀት ኃይል እየተሰማን ነው፣ ሌሊቱ ሌሊት አይመስልም የሆነ ያልተለመድ ብርሃን ነግቶ ይታያል፣ ብዙዎች የንቅልፍ-አልባነት ሰለባ እየሆኑ ነው)፤ ይህን የፀሐይን ክስተት ከሚከተለው የቅዱስ ራጔል ተአምር ጋር እናገናኘው፤
🌞 A Massive Ethiopia-Map-Shaped Sunspot Nearly 50x Larger Than Earth Has Appeared on The Sun
https://axumitethiopia.blogspot.com/2025/11/a-massive-ethiopia-map-shaped-sunspot.html
https://www.bitchute.com/video/943FbpPd8IbX/
🌞 ከምድር ሃምሳ/50 እጥፍ የሚበልጥ ግዙፍ የሆነ እና የኢትዮጵያ ካርታ ቅርጽ ያለው የፀሐይ ጠብታ በፀሐይ ላይ ታየ
😇 አማላጅነቱ ኃይለ ረድኤቱ ለሁላችን ይደረግልንና የመልአክት አለቃ ቅዱስ ራጉኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው፤
እስራኤል ከግብጽ ከወጡ በኋላ እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው ተስፋ የሰጣት ወደ ከነዓን ምድር በገቡ ጊዜ የሃገሪቱን አውራጃውንና ወረዳውን ለይቶ በየነገዳቸውና በየወገናቸው ለእስራኤል ርስትን ያከፋፈለ የነዌ ልጅ ኢያሱ የሚባል አንድ መስፍን ነበረ።
ከእለታት በአንድ ቀን የአምሬውን ነገስታት ኢያሱን ይወጉት ዘንድ የእስራኤል ሕዝብ ወደሰፈረበት በገባዖን ምድር ወደ ገልገላ ተከማቹ። ኢያሱም ይህን በሰማ ጊዜ ከእርሱ ጋር የነበሩት የጦር ሰራዊትና የጦር አለቆችንም ሁሉ ይዞ ሌሊቱን ሁሉ ገስግሶ ድንገት ደረሰባቸው። ኢያሱም ከጠላቶቹ ጋር ገና በተፋፋመ ጦርነት እንዳለ ፀሐይ ልትጠልቅ ተቃረበች ምሽትም ሆነ።
በዚያም ጊዜ ኢያሱ የነዌ ልጅ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ ሕዝብህ እስራኤል ጠላቶቹን ፈጽሞ እስኪያጠፋ ድረስ ፀሐይ በገባዖን ትቅም ዘንድ በኤሎንም ሸለቆ ጨረቃ ይዘገይ ዘንድ አብርሃምን፣ ይስሐቅንና ያዕቆብን አስበህ ፀሎቴን ተቀበል በማለት ጸለየ። ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔርም የነዌ ልጅ የኢያሱን ጸሎት ሰማውና ፀሐይን ከምዕራብ ወደ ምስራቅ መልሶ ባለችበት ፀንታ ትቆም ዘንድ መልአከ ብርሃናት ራጉኤልን አዘዘለት።
የመልአክ አለቃ ቅዱስ ራጉኤልም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ፀሐይን ከምዕራብ ወደ ምስራቅ መለሰውና ፀሐይ በሰማይ መካከል ቆመ አንድ ቀን ሙሉውን ወደ መግቢያው ለመሄድ አልተቻኮለም ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይም ጨረቃም ባሉበት ፀንተው ቆዩ እንጂ።
የመላእክት አለቃ ራጉኤል በፀሐይ በጨረቃና በከዋክብት በሌሎችም ብርሃናት ሁሉ ላይ የሰለጠነ ነውና። መስፍኑ ኢያሱም በጠላቶቹ በገባዖን ሰዎች ላይ ድልን ከተቀዳጀ በኋላ በቅዱስ ራጉኤል መሪነት ፀሐይ ቦታውን አውቆ ወደ መግቢያው ተቀላቀለ። በዚህም ጊዜ መስፍኑ ኢያሱ የነዌ ልጅ በመልአከ ብርሃናት ራጉኤል እጅ ፀሐይን አቁሞ እግዚአብሔር ስላደረገለት ታላቅ ኃይል ፈጽሞ ተደሰተ ፈጣሪውንም አመሰገነ።
🙏 አምላካችን እግዚአብሔር ከነብዩ ኤልያስ በረከቱን ያድለን፣ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል አማላጅነቱ ለሀገራችን ለኢትዮጵያና ለመላው ህዝቦቿ ለዘለዓለሙ በእውነት ይደረግልን፣ ቅዱስ ራጉኤል አጋንንትን የሚያሳድድ የሰይጣናትን ጥፋት የሚበቀልም ነውና ጠላቶቻችንን ሁሉ አሳድዶ ይበቀልልን አሜን!
♰ Founded in 1872, The Addis Ababa St. Raguel and Elijah Church, also known as Kiddus Raguel Church, is a historic Ethiopian Orthodox site on Entoto Mountain (3,200 meters above sea level), famous for its stunning, centuries-old wall paintings made from natural pigments, its unique hand-carved rock-hewn church, and a small museum with relics, offering a glimpse into early Addis Ababa history and Ethiopian art. The Church features beautiful frescoes and a fascinating ancient cave church, making it a key spiritual and cultural landmark.
Key Features & What to Expect:
Stunning Frescoes: The interior walls boast vivid, hand-painted murals depicting biblical stories and saints, some as old as the church itself (around 140 years).
Rock-Hewn Cave Church: A separate, ancient church carved directly into the rock on the same grounds, predating the main wooden structure.
Small Museum: A nearby museum houses historical artifacts like old manuscripts and crosses.
Location: Perched on the scenic Entoto Hills, offering great views.
Living Church: It's an active place of worship, not just a museum, with pilgrims visiting.
😇 One day, as the prophet Elijah was praying, the Angel, the Holy Raguel was revealed and told him, "Rejoice, for the time has come for you to ascend to heaven. You will live in a land of complete happiness. A place where no sickness, death, sorrow, but full of blessing. There is one like you, Enoch, who writes the commandment of the Most High God.
No comments:
Post a Comment